በሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ የፍርድ ቤት የጃናሞራ ወረዳፍርድ ቤት ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያና ሌሎች የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 ህትመት፣ ሎት 3 ጽዳት እቃዎች እና ሎት 4 ኤሌክትርኒክስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የግዥ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በብር የጽህፈትና ሌሎች የጽህፈት መሳሪያ ብር 30 /ሰላሳ ብር/ ህትመት ብር 20 /ሀያ ብር/ ጽዳት ብር 10 /አስር ብር/ ኤሌክትርኒክስ ብር 30 /ሰላሳ ብር/ በመውሰድ ጃናሞራ ወረዳ ፍርድ ቤት ከግዥ ፋይ/ንብ/አሰ ቡድን መሪ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 በመምጣት ገዝተው መውስድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ለሞሉት የጨረታ ዋጋ ማስከበሪያ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ በፖስታ ታሽጎ መቅርብ አለበት፡፡
- በደባርቅ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ህዳር 22/2018 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 06/2018 በጋዜጣ የሚቆይ መሆኑ ታውቆ ተጫራቾች ዘወትር በስራ ስዓት መጥተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ /ፋይ/ን/አሰ ቡድን መሪ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 ታህሳስ 07/2018 ዓ/ም በእለቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፍታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችው ቢገኙም ባይገኙም የጨረታ ስርዓቱ ይካሄዳል፡፡
- ጨረታው የሚከፍትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ላይ ሥርዝ ድልዝ ሊኖረው አይፈቀድም ካለውም ፓራፍ ይደረግበት፡፡
- ተጫራቾች ከሚያስገቡት የጨረታ ሰነድ ፖስታ ላይ የድረጅታቸውን ማህተም ማድርግ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የእቃ እርክክቡ ጃናሞራ ወረዳ ፍርድ ቤት ድረስ ግዥ ፋይ/ንብ/አሰ/ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በማምጣት የሚያስረክቡ ሲሆን የትራንስፖርቱ ወጭ እንዲሁም ማስጫኛና ማውርጃ አስበው መሙላት አለባቸው፡፡
- ለበለጠ መረጃ ጃናሞራ ወረዳ ፍ/ቤት በአካል በመገኝት ወይም ቁጥር 058 294 02 26 /09 18 22 64 89 በመደወል መረጃ ማግኝት ይችላሉ፡፡
- ማሳሰቢያ፡- መስሪያ ቤቱ የጨረታ ውድድሩን በሎት ድምር ወይም በተናጠል ለማድርግ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የጃናሞራ ወረዳ ፍርድ ቤት

