ግልጽ የጨረታ ማስታዎቂያ

0
16

በባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት የደቡብ አቸፈር ወረዳ ፍ/ቤት ለመ/ቤታችን የሚያስፈልግ አመታዊ ግዥ ማለትም ሎት 1. የጽ/መሳሪያ፣ ሎት 2. ህትመት፣ ሎት 3. የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 4. እጅ መሳሪያ እንዲሁም ሎት 5. ቋሚ እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መጫረት የሚፈልግ ማንኛውንም ተጫራች የሚያሟሉ መወዳዳር ይችላል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፡፡
  3. የግዥ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ  አለባቸዉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ዘወትር በሥራ ሠዓት በእያንዳንዱ ሎት የማይመስስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል ደ/አቸ/ወ /ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቢሮ ቁጥር 13 መግዛት ይችላል፡፡
  6. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃዉን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በየምድቡ በተለያየ ፖስታ በማድረግ በጥንቃቄ በማሸግ በደ/አቸ/ወ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ክፍል ቢሮ ቁጥር 13 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላል፡፡
  9. ጨረታው የሚቆየው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ብቻ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛዉ ቀን በሥራ ስዓት ከረፋዱ በ3፡30 ታሽጎ ከረፋዱ 3፡45 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በግልጽ የሚከፈት ሲሆን የሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥስው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 የቅሬታ ቀናት በኋላ በ5 ተከታታይ ቀናት 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ዉል መዉሰድ አለበት፡፡ እንደዉሉ ባይፈፀም ግን የጨረታ ማስከበሪያዉ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  11. የጨረታ ውድድር የሚካሄደው በሎት ጥቅል ድምር ስለሆነ ተጫራቾች ሚወዳደሩበትን ሎት ሁሉንም መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ በጥቅል ድምር አሸናፊ ለሚለይባቸው እቃዎች ለአንድም እቃ ዋጋ አለመሙላት ከጨረታ ውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
  12. መ/ቤቱ በጨረታ ከሚገዛው ዕቃ መጠን እስከ 20 በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
  13. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች ማስጫኛና ማውረጃ አንዲሁም ትራንስፖርት ወጭውን ችሎ ደ/አቸፈር ወረዳ ፍ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡ የጨረታ ሰነዱ ሥርዝ ድልዝ መሆን የለበትም ሥርዝ ድልዝ ከሆነ ፓራፍ መደረግ ይኖርበታል፡፡
  15. በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር 058 223 01 60 በመደወል ቢሮ ወይም ቁጥር 13 በአካል በመምጣት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  16. አሸናፊ የሆነው ደርጅት ለሰነድ ምርምራ አገልግሎት ክፍያ በራሱ የሚከፍል ይሆናል፡፡

የደቡብ አቸፈር ወረዳ ፍ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here