ግልጽ የጨረታ ማስጣወቂያ

0
85

በደቡብ ጎንደር ዞን የአንበሳሜ ከተማ ውሃና ፍሳሽ  አገልግሎት ጽ/ቤት ትራንስፎርመር ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ግዥ ከ200¸000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ከ1-4 ከተዘረዘሩት ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች በድርጅታቸው ስም የተቀረፀ ማኅተም ሊኖር ይገባል፡፡
  7. የሥራውን እና የማሽኑን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ወይም /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለሰ 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል አንበሳሜ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ቢሮ ቀጥር 03 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የሥራና የማሽን አይነት 140,000.00 /አንድ መቶ አርባ ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤቱ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  10. የሚገዙትን የጨረታ ሰነድ ዋጋ በመሙላት እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ በተለያየ ፖስታ ኦርጅናሉን በማሽግ ከፖስታው ጀርባ አንበሳሜ ከተማ ው/ፍ/አ/ጽ/ቤት በማለት ስምና የሚወዳደሩበትን አይነት በመግለጽ ዘወትር በሥራ ሰዓት በጨረታ ሳጥኑ ውስት ማስገባት አለባቸው፡፡
  11. የጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን የጨረታው ሳጥን ከቀኑ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪላቸውን ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል 16 ኛዉ ቀን በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  12. መ/ቤቱ ጨረታውን በሎትም ሆነ በተናጠል የማየት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. መሥሪቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ስለ ጨረታው ዝረዝር ሁኔታ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 258 02 51 /09 23 33 76 20 ወይም ቢሮ ቁጥር 03 በአካል በመገኘት መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአንበሳሜ ከተማ ውሃና ፍሳሽ  አገልግሎት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here