ግልጽ የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

0
111

የአማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት የተለያዩ ያገለገሉ የግንባታ፣ የሳኒተሪ፣ የኤሌክትሪክ፣ የማሽንና ተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎችን ምሥራቅ አማራ ቅ/ጽ/ቤትና ደሴ በሚገኙ ፕሮጀክቶች መጋዝኖች ባሉበት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ዕቃዎቹ ያሉበትን ሁኔታና አይነታቸውን በአካል ተገኝቶ መመልከት ይቻላል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ማንኛውንም ዕቃዎችን ለመግዛት የሚፈልግ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች፣ መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ የልማት ድርጅቶች፣ የመንግስት ተቋማት እና ፋብሪካዎች መሳተፍ የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን ምሥራቅ አማራ ቅ/ጽ/ቤት /ደሴ/ ከተማ ቀበሌ 10 የአማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ፡፡ የዕቃዎችን አይነትና መጠን የያዘ ዝርዝር መረጃ በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ተካቷል፡፡

  1. ተጫራቾች ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን (15 ተከታታይ ቀናትን በመቁጠር) ከቀኑ 8፡00 ድረስ ብቻ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ድረስ ቢሮ ቁጥር 02 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በተዘጋበት ቀን ከቀኑ 8፡30 በድርጅቱ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  3. ከጨረታ ሳጥን መዝጊያ ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  4. በሚቀርበው የጨረታ ሰነድ አካቶ ማቅረብ የሚገባው የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ አስር በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. የጨረታ አሸናፊው ለአሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ አስር በመቶ የመልካም ሥራ  አፈጻጸም ዋስትና /ፐርፎርማንስ ቦንድ/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ማስያዝ ይችላሉ፡፡
  6. የጨረታው ሰነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
  7. የጨረታ ተወዳዳሪዎች ከመነሻ ዋጋ በታች መሙላት አይቻልም ሞልተው የተገኘ ከወድድር ወጪ ይሆናል፡፡
  8. በጨረታ ሠነዱ በእያንዳንዱ ገጽ እና ፖስታው ላይ የድርጅቱ ፊርማና ማህተም ሊኖር ይገባል፡፡
  9. በጨረታው ቅር የተሰኘ ተጫራች የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 የሥራ ቀናት ብቻ ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል፡፡
  10. የጨረታው አሸናፊዎች ንብረቱን በራሳቸው ወጪ ከቦታው ድረስ በመሄድ ቆጥረው ወይም መዝነው ይረከባሉ፡፡
  11.  አሸናፊዎች ዉለታ ከፈረሙ በኋላ የአሸነፉበትን የእቃ ዋጋ ጠቅላላ  ከቫት ጋር ንብረቱን ከመጫናቸው በፊት ቅድሚያ ለድርጅቱ ገቢ ያደርጋል፡፡
  12. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ድርጅቱ ጨረታ ያወጣበትን የዕቃ አይነት የጨረታ ሂደቱ ከመጠናቀቁ በፊት ሊጠቀምበት ከቻለ በእያንዳንዱ እቃ በከፊል ወይም በሙሉ ከጨረታ ሊሰረዝ ይችላል፡፡
  14. ማንኛውም ተጫራች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር 033 311 10 09 /09 24 75 84 87 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አድራሻ ደሴ ካራ ጉቱ ዞን ግብርና ፊት ለፊት

የአማራ ህንፃ ስራዎች ኮንስትራክሽን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here