ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
154

በአብክመ  የአደጋ  መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ለኮሚሽኑ አገልግሎት የሚውሉ 1ኛ.የጽሕፈት መሳሪያ፣ 2ኛ.የሠራተኞች ሰርቪስ እንዲሁም ሎት 1. የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት2. የመኪና ጎማ እና መለዋወጫ፣ ሎት3. ብስክሌት እና የብስክሌት ጎማ ከነካላማዳሪው ሎት4. የፕላስቲክ ማዳበሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ሰርቲፊኬት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የሚገዙ ዕቃዎች ከ200‚000.00 /ከሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-4 የተገለጹትን መስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከሰነዱ ጋር አብረው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች 1.የጽሕፈት መሳሪያ፣ 2. የሠራተኞች ሰርቪስ እንዲሁም ሎት 1. የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት 2. የመኪና ጎማ እና መለዋወጫ፣ ሎት3. ብስክሌት እና የብስክሌት ጎማ ከነካላማዳሪዉ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም ዓይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚገዙት እቃዎች የጠቅላላ ዋጋውን አንድ በመቶ እንዲሁም ለመኪና ሰርቪስ አገልግሎት ለመወዳደር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ.) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሥሪያ ቤቱ የገቢ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን እና ደጋፊ ማስረጃቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ አማርኛ መሆን አለበት፡፡
  10. በጨረታው ለመሳተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጭዎች ቢኖሩ መሥሪያ ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
  11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ሦስት ዓይነት ስለሆነ በሚመለከታችሁ የንግድ ዘርፍ የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ተኛው ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 106/107 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  12. ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ተኛው ተከታታይ ቀን ቆይቶ በ16ተኛው ቀን በ4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸ በተገኙበት በአብክመ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና  ኮሚሽን አዳራሽ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ ህዝባዊ በዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ተጫራቶች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በራሳቸው ምክንያት ባይገኙ ሰነዱ በሌሉበት ይከፈታል፡፡
  13. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም ዓይነት ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 058 218 00 14/ 058 218 11 03 ይደውሉ፡፡
የአ.ብ.ክ.መ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here