ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
142

የአብክመ ገቢዎች ቢሮ ለ2016 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከላይ የተጠቀሱትን ዕቃዎች ለማቅረብ የሚችሉና ህጋዊ የአቅራቢነት ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎች ሁሉ በጨረታዉ እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል።ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች   በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡

  1. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፍኬት የሚያቀርቡ እና ከብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺ ) እና በላይ ለሚጠይቁ ግዥዎች የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ብር የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ብር 30,000.00 ( ሰላሳ ሺ) ብቻ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተመሰከረለት ቼክ /ሲፒኦ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  3. ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለተከታታይ 15  ቀናት በአብክመ ገቢዎች ቢሮ ባህርዳር ቢሮ ቁጥር 313 የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ግዥ የማይመለስ ብር 100.00 ( አንድ መቶ) ብቻ ሰነዱን በመግዛት የነጠላ ዋጋ እና ጥቅል ዋጋ በመሙላት በፖስታ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 313 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ቅዳሜ እስከ 6:30 ጨምሮ ማስገባት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  4. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል፤ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 313 ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም መ/ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብት አለው ፤ በ16ኛው ቀን ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ወይም እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰዉ ሰዓት ይከፈታል። የጨረታው አሸናፊ ማንኛውንም ወጭ ራሱ ችሎ ለቢሮው አሸናፊ የሆነባቸውን ዕቃዎች ያስረክባል።
  6. ቢሮዉ በማንኛውም ሰዓት ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
  7. አድራሻችን፡-ባህር ዳር ቀበሌ 16 ሜድሮክ ግብርና ምርምር ፊት ለፊት ስልክ ቁጥር 0582265765 ወይም 0582266171 በመደወል ማንኛውንም መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡

የአብክመ ገቢዎች ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here