ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
143

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳዳር ማረሚያ ቤት መምሪያ ለህግ ታራሚዎች ለምግብ አገልግሎት ሎት1.የባልትና ውጤቶች፣ሎት2. የፋብሪካ ዉጤቶች፣ ሎት3. የማገዶ እንጨት፣ ሎት4. ፊኖ ዱቄት፣ ሎት5. አትክልት፣ እንቁላልና የቅባት እህሎችን  በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውና ከመንግሥት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው ለመሆናቸው ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ከ200,000.00 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ሽያጭ ለሚፈፅሙ አቅራቢዎች ቫት ከማይጠየቅባቸው ውጭ ባሉት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ፡፡
  3. ተጫራቾች በሥራ ፈቃዳቸው መሰረት ማቅረብ የሚገባቸውን ለይተው በመሙላት በታሸገ ፓስታ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ከጨረታ መክፈቻው ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች ለመወዳደር ባቀረቡባቸው እቃዎች የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉበትን ሎት1. 50,000.00 /ሃማሳ ሺህ ብር/፣ ሎት2. 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/፣ ሎት3. 50,000.00 /ሃማሳ ሺህ ብር/፣ ሎት4. 50,000.00 /ሃማሳ ሺህ ብር/፣ ሎት5. 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ፣ በጥሬ ገንዘብ እና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረበ አለባቸው።  አሸናፊው ውል ሲይዝ የውል ማስከበሪያ እና የጨረታ ማስከበሪያ  ገንዘብ በመጨመር  የሚያስዝ ሆኖ ለተሽነፈ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያው የሚመለስለት ይሆናል፡፡
  5. ከ10,000.00 /ከአስር ሺህ ብር / በላይ ለሆነ ሽያጭና የሽያጭ ታክስ ከሚከፈለው ጠቅላላ ገንዘብ ላይ በመመሪያው መሰረት ሁለት በመቶ መክፋል ይኖርበታል፡፡
  6. በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መሙላት አይቻልም፡፡
  7. ተጫራቶች የጨረታ ሰነዳቸውን ኦሪጅናልና ኮፒ በመለየትና በተለያዩ ፖስታ በማሽግ ሰነዱ ላይ ፊርማ እና የድርጅታቸውን ማህተም ማሳረፍ አለባቸው፡፡
  8. የጨረታ አሸናፊዎች ውጤቱ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ በማስያዝ ውል ይዘው ያሸነፋባቸውን እቃዎች በባሕር ዳር ማረሚያ ቤት መምሪያ ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ ተጫራቶች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥ ፋይናስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ በ16 ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡ መምሪያው ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ  መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 058 320 31 39፣ 09 18 08 20 16፣ 09 18 13 48 43 ደውለው ወይም በአካል ባሕር ዳር ማረሚያ ቤት መምሪያ ግዥ/ፋስ/ንብ/አስ/ሥራሂደት በመምጣት መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

የባሕር ዳር ከተማ አስ/ ማረ/ ቤት መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here