ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
118

የጭልጋ ወረዳ ማረሚያ ቤት አስ/ጽ/ቤት በበጀት ዓመቱ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡  ሎት 1. የምግብና እህል፣  ሎት 2. የወጥ ማጣፈጫ፣ ሎት 3. የምግብና ዘይት፣ ሎት 4. የማገዶ እንጨት፣ ሎት 5. አትክልት እና ፍራፍሬ  የሕግ ታራሚዎችን ለመመገብ አሸናፊው ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ ለስድስት ወራት ከተቋሙ ድረስ የሚያቀርብ ተጫራቾችን ጽ/ቤቱ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. የዘመኑን የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/የሚያቀርቡ፡፡
  4. የግዥው መጠን ከ200‚000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸወን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ 50.00 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል ለግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 05 ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ የሚሞሉትን አንድ በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፕኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት የአሸነፈውን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፕኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  9. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት የአሸነፈውን እቃ ጭልጋ ማረሚያ ቤት መጋዝን ድረስ የሚያቀርብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ቅጅዎች ማለትም ዋናውንና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የጭልጋ ወረዳ ማረሚያ ቤት አስ/ጽ/ቤት ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን መሪ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በተከታታይ 15 ቀናት ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ከ22/11/2016 እስከ 12/12/2016 ዓ/ም አስከ 11፡30 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው ሳጥን በ13/12/2016 ዓ/ም ከጥዋቱ 4፡00 ላይ ይታሸጋል፡፡
  11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን መሪ በ13/12/2016 ከጥዋቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡
  12. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃና ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 333 00 09 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
  14. በሎት የተዘረዘሩት እቃዎች በጥቅል ዋጋቸው አሸናፊው ይለያል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ያገኛሉ፡፡

የጭልጋ ወረዳ ማረሚያ ቤት አስ/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here