የላይ አርማጭሆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2016 በጀት ዓመት ለወረዳው ሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት ለሚሰጡ መኪኖች የመኪና መለዋወጫ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ዓመታዊ ኩንትራት ግዥ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች ጋዜጣው ከወጣበት እስከ 15ኛው ቀን ድረስ ሰነዱን በላይ አርማጭሆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመግዛት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 3፡30 ታሽጎ በ4፡00 በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ዝርዝር መረጃውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ከሚገኘው ማስታወቂያ ማግኘት ይቻላል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የላይ አርማጭሆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት