ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
154

በደቡብ ወሎ ዞን በተንታ ወረዳ የአጅባር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ የደንብ ልብስ፣ የጽሕፈት መሳሪያ አሌክትሮኒክስ፣ ኤሌክትሪክ ሲቲ እና ህንጻ መሳሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆንም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማለትም፡-

  1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው ለመሆኑ ማረጋገጫ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግዥ መጠን 200,00000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር /እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምሰክር ወረቀት ማቅረበ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. የሚገዙትን እቃዎች አይነት ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማገኘት ይቻላል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 /ሁለት በመቶ ብር/ በመክፈል ከአጅባር ፖሊ ኮሌጅ ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/ስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 1 ማገኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ፤ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመሥሪያ ቤቱ ሕጋዊ ደረሰኝ ገቢ ተደርጎ ካርኒው ከሰነዱ ጋር አብሮ ከሳጥኑ ውስጥ መግባት አለበት፡፡ ደረቅ ቸክ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  7. አሽናፊው የሚለየው በጥቅል /በሎት/ ዋጋ በመሆኑ ተጫራቾች ሁሉንም ዝርዝር ዋጋ መሙላት አለባቸው፡፡
  8. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን በኋላ የውል ማስከበሪያ ካሸነፈበት ከጠቅላላ ዋጋ ሃያ አምስት በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአጅባር ፖሊ ቴክ/ኮሌጅ ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ በ4፡00 በይፋ ይከፈታል፡፡ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ አጅባር ፖሊ ቴክ ኮሌጅ ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን 3፡30 ድረስ ማስገባት ይቻላል፡፡
  11. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈውን እቃ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ድረስ በራሱ ወጭ ማቅረብ አለበት፡፡ በተጨማሪም የሚቀርቡ እቃዎች በባለሙያ እየተረጋገጠ የምንረከብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  12. የሚገዙ እቃዎች አይነት እና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡ እንዲሁም የሚጠየቁትን ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  13. በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ መሞላት አለበት፡፡ ሆኖም ስርዝ ድልዝ ካለው ስለመስተካከሉ ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
  14. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. መሥሪያ ቤቱ በጨረታው በቀረቡ እቃዎች መጠን ሃያ በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
  16. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ግዥ ክፍል ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 441 04 70 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
  17. በዚህ ጨረታ ያልተገለፁ ጉዳዮች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡

የአጅባር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጁ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here