ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
139

የአብክመ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በኢንስቲትዩቱ ግቢ ዉስጥ ዘመናዊ ጂ+1 /G+1/ ወርክ ሾፕ እና ቢሮ ህንፃ ግንባታ ሥራ በሥራ መስኩ ህጋዊ የግንባታ ፈቃድ ያላቸዉን ተቋራጮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መሰፈረቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡
በዘመኑ የታደሰና በግንባታ ዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው /ቲን/ እና ተከታታይ ደረሰኝ ያላቸው፡፡
ከከተማ ኮንስትራክሽን እና ልማት ቢሮ የታደሰ ፈቃድ ያላቸው፡፡
የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ደረጃ 7 እና በላይ መሆናቸዉን የሚያሳይ የታደሰ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና ሌሎች በዘርፉ የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
የግንባታዉን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአማረኛ ቋንቋ ሥርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያው ሰነድ መሰረት የአንዱን ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ድምር ዋጋ በሞሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ኦርጅናል እና ኮፒ ለብቻዉ በፖስታ በማሸግ በኢንስቲትዩቱ ግቢ ዉስጥ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ የከተማ ኮንስትራክሽንና ልማት ቢሮ የግንባታ መመሪያ በሚያዘዉ መሰረት በግንባታዉ ላይ አስፈላጊዉን ማሻሻያ ወይም የለዉጥ ሥራ ሊያሰራ ይችላል፡፡
ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 04 ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መዉሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000.00 /ሃምሳ ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ / ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የኢንሹራንስ ጋራንቲ ብቻ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 /ሃያ አንድ/ ቀናት በአየር ላይ ከዋለ በኃላ በ22ኛዉ ቀን ጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 3፡40 ላይ ይከፈታል፡፡
የጨረታው አሸናፊዎች የሚለየው በመሀንዲስ የሂሳብ ስሌት /አርቲሜቲክ ቸክ/ መሰረት ይሆናል፡፡
ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 32 38 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
ኢንስትትዩቱ የሚሰበስበው ሁለት በመቶ ዊዝ ብቻ ነዉ፡፡

የአብክመ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here