ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
100

የግዥ መለያ ቁጥር 18/2017

ሱታና ንግድና የማማክር ስራዎች ኢትርፕራይዝ ለተማሪዎች ለምግብ አግልግሎት የሚውል  ጥራቱን የጠበቀ ቀጭ ቀጭ የሌለው ነጭ ጤፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ስለሆነም በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርቶች መሰረት በማድረግ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገልጽን ፡፡

  1. አድራሻ በአማራ ብሔራዊ ክልልዊ መንግስት በአዊ አስ/ዞን እንጅባራ ከተማ እንጅባራ ዩኒቨርስቲ ሱታና ንግድናየማማከር ስራዎች ኢተርፕራይዝ ነዉ፡፡
  2. በጨረታዉ መወዳደር የሚችሉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ ብቻ ናቸዉ ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል ከሱታና ንግድና የማማክር ስራዎች ኢተርፕረይዝ ስራ ክፍል በመዉሰድ ዋጋ በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ኢንቨሎፕ /ፖስታ/የድርጅቱን ስምና ማህተም በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት ለይቶ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ከጨረታ መዝጊያ ቀን በፊት በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ኢትርፕራይዙ ብሎክ 2 ቢሮ ቁጥር 203 የምትጫረቱትን የአንዱን ዋጋ በመሙላት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ተመዝጋቢ ከሆኑ ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸዉ የሚገዛዉ ዕቃ ከ200,000.00/ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ የሚሆን ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ አቅራቢ ድርጅቶች ብቻ የሚወዳደሩ ይሆናል ፡፡ የጨረታ አሸናፊዉ ያሸነፈውን ጤፍ የወዛደር ማወረረጃን ጭምር ራሱ ችሎ ዩኒቨርስቲዉ ግቢ ድረስ በራሳቸዉ ወጭ  በማቅረብና ማስረከብ አለባቸዉ ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲመልሱ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000/መቶ ሽህ ብር/ ብቻ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በመክፈል ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  6. የጨረታዉ አሸናፊ የዉል ማስከበሪያ ገንዘብ 10% በጥሬ ገንዘብ ወይም /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
  7. የጨረታ አሸናፊዉ ያሸነፋቸዉ ውል መያዝ አለባቸዉ፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱ ማስገባት የሚጀምረዉ ማስታወቂያዉ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን ጨረታዉ በ16 ኛዉ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ከጥዋቱ 4፡00ታሽጎ በዚያዉ ቀን በ4፡30 ይከፈታል ፡፡የጨረታ መክፈቻዉ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል ፡፡ነገር ግን በጨረታ መክፈቻ ሰዓት አቅራቢዎች ወይም ወኪሎች ባይገኙም በጨረታ አከፋፈት ስርዓቱ ተገዥ ይሆናሉ ፡፡ ሰነዱን የወሰዱት ሁሉም ተጨራቾች ከመክፈቻ ቀን በፊት ሁሉም ከመለሱልን የመክፈቻ ቀን ሳንጠብቅ የምንከፍት ይሆናል፡፡
  9. አሸናፊዉ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ከ7 /ሰባት/ቀን በኃላ ባሉት 8 ቀናት ዉስጥ ዉል መያዝ አለባቸዉ ፡
  10. ኢተርፕራይዙ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  11. 11 ኢተርፕራይዙ 20% የመቀነስ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
  12. ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 -11 -59 -13 -56 ወይም 09 -13- 42 -26 -44 ይደዉሉ፡፡

ሱታና ንግድ ና የማማከር ስራዎች ኢተርፕ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here