ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
108

በምሥራቅ ጎጃም ዞን የግንደወይን ከተማ አስተዳደር ከተማ ገንዘብ /ጽ/ቤት ለግ/ወይን ከተማ ለተለያዩ ሰፈሮች አገልግሎት የሚውል ትራንስፈርመር አቅርቦት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  4. የግዥው መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለማሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመልስ00 /ሁለት መቶ ብር/ በመግዛት የጨረታ ሰነዱን ከመ/ቤታችን ረዳት ገንዘብ ያዥ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ 300,000.00 /ሶስት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዛ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዝብ ገቢ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና  ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማለትም ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ዘወትር በሥራ  ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ገንዘብ/ጽ/ቤት ኃላፊ ቢሮ ቁጥር 1 /አንድ/ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጐ 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ተጫራቾች በጨረታው ያወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን የማይወስድ መሆኑ ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
  12. አሸናፊ ድርጅቱ ያሸነፈባቸውን ማቴሪያሎች ከተማ አስተዳደሩ ድረስ በራሱ ትራንስፓርት ወጭ ማቅረብ የሚችል፡፡
  13. መ/ቤቱ የጨረታ አሸናፊውን በጥቅል  ዋጋ  ይለያል፡፡
  14. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ ቀን ጀምሮ አቤቱታ /ቅሬታ/ ካላቸው በተከታታይ 5 /አምስት/ የሥራ ቀናት ቅሬታ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ከ5 /አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውጭ የመጣ ቅሬታ ጽ/ቤቱ የማይቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  15. መ/ቤቱ ከአሸናፊ ድርጅቱ ያሸነፋቸውን እቃዎች ሃያ በመቶ ከውል በፊት የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. እቃዎች በባለሙያ እየተረጋገጡ ርክክብ የሚፈፀም ይሆናል፡፡
  17. የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በዓል፣ ቅዳሜ እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት መሆኑን ጽ/ቤቱ ይገልፃል፡፡
  18. አሸናፊው ድርጅቱ አሸናፊነቱ ከተገለጸለት ከ5 የሥራ ቀናት በኃላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናቶች ውስጥ መጥቶ ውል በመያዝ የውል ማስከበሪያ አስር በመቶ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  19. ከአሸናፊው ድርጅት ሁለት በመቶ የቅድመ ግብር የሚቆረጥ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  20. ግዥ ፈፃሚው አካል ግዥውን ለመገምገም፣ ለማፅደቅ፣ አቤቱታ ቢነሳ ለማስተናገድ እና አሸናፊ ድርጅቱ ጋር ውል እስገሚገባ ድረስ የመጫረቻ ሰነዱ ጸንቶ የሚቆየበት ለ40 ቀን ይሆናል፡፡
  21. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት ወይም በስልክ በቁጥር 058 861 26 15 በመደወል ዝርዝር መረጃውን ማግኘት ይቻላል፡፡

የግንደወይን ከተማ አስተዳደር ከተማ ገንዘብ //ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here