ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
164

የደቡብ ጐንደር አስተዳደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ2016 በጀት ዓመት ለመስሪያ ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች እና ሎት 2. የላፕቶፕ ቦርሳ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል:: ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የጻሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ::

  1. ተጫራቾች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉና በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተመዘገቡ መሆን አለባቸው::
  2. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
  3. የሎቱ ከጠቅላላ ዋጋ ከ200,000.00 (ከሁለት መቶ ሽህ) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል::
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ከጠቅላላ ዋጋው ላይ አንድ በመቶ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው::
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ደ/ጐን/አስ/ዞን/ከፍ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 35 በመቅረብ ማስያዝ ይችላሉ::
  6. የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሠነዱ ጋር በፖስታ ውስጥ አሽጐ ማቅረብ ከጨረታ ውድድር ውጭ ይደረጋል፤ ገንዘቡም ቢጠፋ መስሪያ ቤቱ ሊጠየቅ አይችልም::
  7. መሥሪያ ቤቱ ለመግዛት የሚፈልጋቸውን እቃዎች ዓይነት እና ዝርዝር የያዘ ሠነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ሦስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 35 በመምጣት እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ ብር 50.00 (ሃምሳ ) በመግዛት መውሰድ ይችላሉ::
  8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ፖስታ አድርገው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቢሮ ቁጥር 35 በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት የሚቻል ሲሆን የጨረታ ሳጥኑም በ15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ይታሸጋል::
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: ወኪሎች ቢገኙም ባይገኙም ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት በአስራ ስድስተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ቢሮ ቁጥር 35 ይከፈታል::
  10. አሸናፊው ድርጅት የሚመረጠው ወይም የሚለየው በጥቅል ዋጋ ወይም በሎት ነው:: የተጠየቁት እቃዎች ሙሉ በሙሉ መሞላት አለባቸው::
  11. አሽናፊው ድርጅት የአሸነፈውን እቃ ደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድረስ አጓጉዞ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት::
  12. ተጫራቾች ሰነድ በሚገዙበት ጊዜ ኦሪጅናል እና ኮፒ ፍቃድ በመያዝ ሰነዱን በአካል ወይም በሕጋዊ ወኪሎዎቸው አማካኝነት ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
  13. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  14. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 03 86 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::

የደቡብ ጐንደር አስተዳደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here