ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
104

የምሥራቅ ጐጃም ዞን ከፍ/ፍቤት ግዥ ፋ/ን/አስ/ቡድን ለመ/ቤታችን አገልግሎት የሚውል 1. የተዘጋጁ ልብሶች፣ 2. የጽህፈት መሣሪያ ዕቃዎች፣ 3. ህትመት፣ 4. የጽዳት ዕቃዎች፣ 5. ኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች፣ 6. የመኪና እቃዎች፣ 7. የመዝገብ መደርደርያ ፣የቢሮ በሮች ፣የችሎት መቋሚያ ክፍል ፣የብረት ካዘናና የሽንት ቤት የመግቢያ በር ፍርግርግ እንዲሁም 8. የኤሌክትሪክ እቃዎች እና የቤት እቃዎች ማስዋቢያ ለማሰራት በጋዜጣ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-

  1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት /ቲን/ ያላቸው፡፡
  3. ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግይ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. የሚገዙት እቃዎችን አይነት ዝርዝር መግለጫ የያዘ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ከላይ የተጠቀሱትን እቃዎች ሰነድ ከምሥ/ጐጃም ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ከግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ ቡድን ከዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ በመምጣት 00 /ሃያ ብር/ በመግዛት መውሰድ ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃዎች ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ከግዥ ቢሮ ቁጥር 103 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይቻላል፡፡
  9. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ ወዲያውኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡
  10. አሸናፊው ከአሸነፈበት ከጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ  የውል ማስከበሪያ ማስያዝ  ይጠበቅበታል፡፡
  11. አሸናፊው እቃዎችን ምሥ/ጐጃም ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ቢሮ ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይጠበቅበታል፡፡
  12. ሃያ በመቶ መቀነስም ሆነ መጨመር የምንችል መሆኑን እየገለጽን ነገር ግን መ/ቤቱ የተሻ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. የጨረታ መክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡ በዚህ ያልተጠቀሱ በግዥ መመሪያው የተቀመጡ የተጫራቾች መመሪያ ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡
  14. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 103 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 771 55 50 መጠየቅ ይቻላል፡፡

የምሥራቅ ጐጃም ዞን ከፍ/ፍ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here