በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የስማዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስተዳደር ቡድን በ2017 በጀት ዓመት ለስማዳ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ በመደበኛ በጀት በካልም በጀት ፣በሪድ ፕላስ በጀት ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ ፣ሎት 2. የግንባታ እቃዎች፣ ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ ፣ሎት 4. የውሃ እቃ ፣ሎት 5 የጽዳት ዕቃ ፣ሎት 6 የመኪና እና የሞተር ጎማ ፣ሎት 7 የተዘጋጀ ፈርኒቸር ፣ሎት 8 የስፖርት ዕቃ ፣ሎት 9 ብሎኬት ፣ሎት 10 የተዘጋጁ ልብሶች ፣ሎት 11 የሙጌ አሸዋ ፣ሎት 12 የተከሰከሰ ጠጠር እና ሎት 13 ጥቁር ድንጋይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ማሟላት የሚፈለግባቸው መስፈርቶች፡-
- ህጋዊ ወቅታዊ የታደሰ በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ቲን ካርድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዳቸውንና ሌሎች መረጃዎቻቸውን በፖስታ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በስማዳ ወረዳ ግ/ን/አስ/ደ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 26 ለሥራው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሃብ ስማቸውን ፣ፊርማቸውን ማህተማቸዉንና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡
- የጨረታው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሣብ ላይ ለውጥ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው እራሣቸውን ማግለል አይችሉም ሥርዝ ድል ፍፁም የተከለከለ ነዉ፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆኑና ለወደፊቱም በመንግስት የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፉ የሚደረጉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች ለሥራው የተዘጋጀውን ሠነድ የማይመለስ00 /አምሳ ብር/ ብቻ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ስ/ወ/ገ/ያዥ ቢሮ ቁጥር 12 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ለዋና ገንዘብ ያዥ ማስያዝና ያስያዙበትን ኮፒ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ አስር በመቶ የውል ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ማቅረብና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
ለበለጠ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር 058 667 01 67 ደውሎ ወይም ግ/ን/አስ/ቡድን በአካል ጠይቆ መረዳት ይቻላል፡፡
የስማዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት