በደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር የነፋስ መውጫ /ፖ/ቴ/ ኮሌጅ ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ሎት1. የፅህፈት መሳሪያ፣ ሎት2. ሕንፃ መሳሪያ፣ሎት3. ኤሌክትሮኒክስ ፣ ሎት4.የግብርና እቃዎችን፣ ሎት5. የሆቴል ማሰልጠኛ እቃዎች ፣ ሎት6. ሶስት ኩንታል የሚመዝን የብር ማስቀመጫ ካዝና መግዛት ይፈልጋል ፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- ህጋዊ ንግድ ፍቃድና /ቲን/ ያላቸው ፎቶ ኮፒውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000.00/ ሁለት መቶ ሽህ/ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት መወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸዉ ስልክ ጨምሮ የድርጅታቸውን ማህተም መኖር አለበት፡፡
- ጨረታው ከተዘጋጀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ የማይቻልና ከጨረታ ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆኑና ለወደፊቱም በመንግስት መ/ቤት ጨረታ የማይሳተፉ ይሆናሉ፡፡
- ጨረታው ከተጫራቾች ውስጥ አሸናፊ የሆነውን ድርጅት በውሉ መሰረት ነፋስ መዉጫ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ድረስ እቃዉን ማስረከብ አለበት፡
- ጨረታው ተከፍቶ እንዳበቃ ከአምስት ቀናት በኋላ ለተከታታይ 5 ቀናት ውል ይሰጣል፡፡የውል ማስከበሪያ በመመሪያው መሰረት የዋጋውን 10 በመቶ ይሆናል፡
- ጨረታው የሚከፈተው በጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ3፡00 ተዘግቶ በ4፡00 ይከፈታል፡
- ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ስለ ጨረታው ሰነድ ማብራሪያ የሚያስፈልገው ከሆነ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ካለው ተቀባይነት የለውም፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ድርጅቱ በውሉ መሰረት እቃዉን ባያቀርብ በውሉ በተመለከተው የገንዘብ መጠን ላይ በየቀኑ1 ወይም 1/100 መቀጫ እንዲከፍል ይደረግና በዚህ አይነት የሚታሰበው የውሉ ዋጋ አስር በመቶ መብለጥ የለበትም፡፡
- ውሉ እንዲፈፀም መዘግየት በስራው እንቅስቃሴ ላይ ተጽእኖ የሚያስከትል ከሆነ የመንግስት መስሪያ ቤቱ በመቀጫው መጠን አስር በመቶ እስኪሞላ ድረስ መጠበቅ ሳይገደድ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውሉን መሰረዝ ይችላል ፡፡
- ኮሌጁ በጨረታ ካሸነፈው ተጫራቾች ላይ 20 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት አላቸው፡፡
- ኮሌጁ አሸናፊውን የሚለየው በነጠላ ዋጋ ነው፡፡
ማሳሰቢያ ፡- ውል ከወሰዱበት የጊዜ ገደብ ውስጥ እቃውን ባያስገቡ በውሉ መሰረት የሚቀጡ መሆኑን እየገለፅን ለ2ኛ አሸናፊ ይሰጣል ወይም ኮሌጅ ለስራ በሚያመቸው መንገድ የምንሰራ መሆኑን ተገንዝበው በተባለው ጊዜ ብቻ እንዲያቀርቡ እንገልፃለን፡፡
የነፋስ መውጫ /ፖ/ቴ/ ኮሌጅ