በምዕራብ ጎጃም ዞን የቡሬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ውስጥ የሚገኘውን ቁርጥራጭ ብረታ ብረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው የምትሳተፉ ድርጅቶች /ግለሰቦች/ በቀረበው የጨረታ ዝርዝር በንግድ ፈቃዱ መሰረት መወዳደር ይችላሉ፡፡ ስለሆነም፡-የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን፣ ተወዳዳሪዎች
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው ከ200,000.00 ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ግዥውን ግምታዊ ዋጋ መሰረት በማድረግ 50,000.00 (አምሳ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ /ሲፒኦ/ በኮሌጁ ስም ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ መቆያ ጊዜ ከ 03/06/2017 ዓ.ም እስከ 17/06/2017 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት ብቻ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን አንድ ወጥ በሆኑ የጨረታ መወዳደሪያውን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቡሬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በግዥፋ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 18/06/2017 ዓ.ም እስከ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን በ16ኛው ቀን ማለትም 18/06/2017 ዓ.ም ሲሆን ከረፋዱ 4፡00 የጨረታ ሳጥን ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በ 18/06/2017 ዓ.ም በእለቱ በ4፡30 ጨረታው የሚከፈት ሁኖ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው በሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ስልክ ቁጥር 058 774 07 71 ደውሎ ወይም በአካል ቀርቦ /ማየት/ መረዳት ይቻላል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ውል ከያዘ በኋላ የሚጠበቅበትን ክፍያ በመክፈል ንብረቱን መረከብ ይኖበታል፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅት /ግለሰብ/ ማሸነፉን በተገለፀ ከአምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት በኃላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውል ካልያዘ የጨረታ ማስከበሪያው ውርስ ይሆናል፡፡
- ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተገለፁ ነገሮች ካሉ በግዥ መመሪያው መሰረት ተግባራዊ ይሆናሉ፡፡
- አሸናፊ ድርጅቱ /ግለሰቡ/ የሚዛን እና ሌሎች ወጭዎች በራሱ ሂሳብ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከኮሌጁ ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 የማይመለስ በ400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይቻላል፡፡
የቡሬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ