ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
80

የባህር ዳር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በግቢው ውስጥ የሚገኙትን ቆርቆሮ በቆርቆሮ የተሰሩትን 2  ብሎኮችን በእጅ ዋጋ ብቻ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ በጫረታው መሳተፍ ትችላላችሁ።

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. ጨረታው ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ የማይመለስ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. እያንዳንዳቸውን እቃ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100 /አንድ በመቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 17 የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ጨረታውን በሚሞላበት ጊዜ በተጠየቀው መለኪያ መሰረት መሙላት ይጠበቅቦታል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወደደሩበት እቃ ጠቅላላ ዋጋ ብር አንድ በመቶ በኮሌጁ ስም በተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ማስያዝ እንዲሁም በጥቃቅን የሚወዳደሩ ከሆነ ከኢንተርፕራይዝ ቢሮ የድጋፍ ማስረጃ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. የመልካም ሥራ አፈፃፀም ቢያንስ 2 ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው በሚሞሉበት ወቅት ሥርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
  11. ጨረታው የሚዘጋው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ይቆይና በ16ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጐ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያው እለት 4፡15 ይከፈታል፡፡ ሆኖም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  12. ኮሌጁ ጨረታውን በጥቅል ዋጋ የማወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ኮሌጁ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር እና ፋክስ ቁጥር፡- 058 218 0574 ደውለው መጠየቅ ይችላል፡፡

ማሳሰቢያ፡- በጨረታው መሳተፍ የሚችሉት ከደረጃ 1 አስከ ደረጀ 9 ብቻ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የባህር ዳር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here