ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
82

የጉና በጌምድር ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት የግዥ ቡድን ለጉና በጌምድር ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ በመደበኛ በጀት እና በፕሮጀክት በሰቆጣ ቃል ኪዳን በጀት ሎት 1.የግንባታ እቃዎች ፣ ሎት 2. ስሚንቶ ሎት 3.የስፖርት ማቴሪያል  እና አልባሳት ፣ ሎት 4. የውሃ እቃ በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳዳር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  3. የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ጨረታው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ በጉና በጌምድር ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 17 በመምጣት   ለእያንዳንዱ የማይመለስ 50 ብር /አምሳ/ ብር ብቻ በመክፈል ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ጨረታው የሚከፈተው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል ፡፡ ተጫራጮች በጨረታ ሂደቱ ላይ ቢገኙም ባይገኙም ከመክፈት አያግድም፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪ ዋስትና የምታስይዙት በቁርጥ የግንባታ እቃው ብር 8,000 /ስምንት ሽህ/ ብቻ ስሚንቶ የጨረታ ማስከበሪያ 5,000 /አምስት ሽህ ብር/ ብቻ እንዲሁም የስፖርት ትጥቅ 1,500 /አንድ ሽህ አምስት መቶ/ ብር እንዲሁም የውሃ እቃ 8,000/ስምንት ሽህ ብር ብቻ  በባንክ በተረጋገጠ ስፒኦ እና በጥሬ ገንዘብ  በመሂ -1 በማስቆረጥ በማስያዝ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  8. ተጫራቸች በባንክ ያስያዙትን ማስረጃ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከመ/ቤታችን ገቢ ያደረጉበትን የገቢ ደረሰኝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አሽገው ጉ/በ/ወ/ገንዘብ ፅ/ቤት ብለው በመቁረጥ በዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሳጥን ቢሮ ቁጥር 17 ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 16 ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4:30 ይከፈታል፡፡
  9. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆነ ኦሪጅናል /ዋና/ በታሸገ ፖስታ ጉ/በ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 17 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይቻላል፡፡
  10. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከመ/ቤቱ ቀርቦ ባሸነፈበት ገንዘብ መጠን የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መውሰድ ያለበት ሲሆን በወቅቱ ቀርቦ ውል ካልወሰደ በግዥ መመሪያው 1/2003 መሠረት አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል፡፡
  11. የሚገዙትን እቃዎች ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን ከመጫረቻ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  12. እቃው የሚቀርበው ወይም ርክክቡ የሚፈፀመው በሙያተኛ ተረጋግጦ ጉና በጌምድር ክምር ድንጋይ ከተማ በእየ ሴክተር መ/ቤቶች ባሉት ንብረት ክፍል ድረስ ነው፡፡
  13. የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የባዕል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  14. የጨረታው አሸናፊው የሚለየው በሎት መሰረት በሎት ድምር/ በጥቅል ድምር ነው፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  16. ለበለጠ ማስረጃ በስልክ ቁጥር 0582510226 ደውለው ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የጉና በጌምድ ገንዘብ ጽ/ቤቱ

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here