ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
91

በምሥራቅ ጎጃም ዞን የእና/እና/ወረዳ የደብረ ወርቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ 1ኛ.የጽህፈት መሳሪያ እና 2ኛ.የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-

  1. የዘመኑን ግብር የከፋሉና ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠናቸው ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ሲመጡ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነት ዝርዝር መግለጫ /ሰፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች ሰነዱን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ዕቃ የሚሞሉበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመሂ1 ገቢ አድርገው መሂውን ማያያዝ አለባቸዉ፡፡
  8. ተጫራቾች አሸናፊነታቸዉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀን ዉስጥ የዋጋዉን አስር በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ዉል መፈረም አለባቸዉ፡፡
  9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀን ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ላይ የጨረታው ሳጥኑ ታሸጎ በዚሁ ቀን በ4፡30 ላይ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ እለቱ የበዓል ቀን ከሆነ /ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ጨረታው ይከፈታል፡፡
  10. የጨረታው አሸናፊ የእቃዎችን አጠቃላይ የትራንስፖርት ወጭ በመሸፈን ማቅረብ አለበት፡፡
  11. ኮሌጁ አንደ አስፈላጊነቱ በሎትም ሆነ በነጠላ ዋጋ የማወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  12. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  13. ስለ ጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በኮሌጁ ጊዜያዊ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 22 71 63 01 /09 35 48 41 11 /09 20 75 78 75 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

የደብረ ወርቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here