ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
91

የአማራ ልማት ማህበር /አልማ/ ለ583 ሰራተኞች እና ለ1476 የሰራተኛ ቤተሰቦች የህክምና እና የህይወት ኢንሹራንስ ተጠቃሚ ማድረግ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በሁሉም አማራ ልማት ማህበር (አልማ) ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች ማለትም በባህር ዳር፣ በፍኖተ ሰላም፣ በደብረ ማርቆስ፣ በጐንደር፣ በደብረ ታቦር፣ በወልደያ፣ በደሴ፣ በደብረ ብርሃን፣ በአዲስ አበባ ከተሞች ቢሮ ጽ/ቤት ያላቸውን ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ በመጋበዝ ለሦስት ዓመት የህክምና እና ህይወት ኢንሹራንስ መግባት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1 እና 2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተጠቀሱት የማህበሩ ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች ባሉበት ከተማ ቢሮ ጽ/ቤት ያላቸው ለመሆኑ የሚያረጋግጥ የፅሁፍ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ባህር ዳር በሚገኘው አልማ ዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 108 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከቢሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች ፋይናንሻል ሰነድ ለብቻ በማዘጋጀት ያለምንም ሥርዝ ድልዝ መረጃውን በትክክል በመሙላት፣ ከላይ የተጠቀሱትን ነጥቦች መሠረት በማድረግ የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነዶች ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ሰነዶችን ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎኘ በማድረግ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ሰነዶችን ለመለየት እንዲቻል በግልጽ ፅሁፍ ኤንቨሎፑ ላይ በመፃፍ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአማራ ልማት ማህበር /አልማ/ ዋናው መ/ቤት ባህር ዳር ቢሮ ቁጥር G-03 ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው። ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ላይ ይታሸጋል፡፡ በእለቱ በ9፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
  8. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር G-03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 73 60 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአማራ ልማት ማህበር (አልማ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here