የምዕራብ ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለምዕ/ጎጃም ዞን መምሪያዎች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎችን በስድስት ሎት በማደራጀት ማለትም ሎት 1 ጽ/መሳሪያ፣ ሎት 2 የፕሪንተርና የፎቶ ኮፒ ቀለም፣ ሎት 3 ፈርኒቸር፣ ሎት 4 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 5 ኤሌክትሮኒክስ እና ሎት 6 የቀላል መኪኖች ጎማ በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ ህጋዊ አቅራቢዎችን በመጋበዝ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ ጋር በተያያዘው የዋጋ መሙያ ዝርዝር ስፔስፊኬሽን እና ሳፕል መሠረት ዋጋ በመሙላት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የሚመረጠው ከሎት 5 ከኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በስተቀር በቀረበው ዝርዝር መሠረት በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ድርጅት ነው፡፡ አንድም ዋጋ አለመሙላት ከጨረታ ውድድር ውጭ ያስደርጋል፡፡ ሎት 5 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች አሸናፊ የሚለየው በተናጠይል ባቀረቡት ዋጋ ዝርዝር ዝቅጠኛ ያቀረበው ሲሆን በጥቅል ድምር አሽናፊ ለሚለይባቸው ዕቃዎች ለአንድም ዕቃ ዋጋ አለመሙላት ከጨረታ ውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 /አምሳ ብር/ የሚሽጥ ሲሆን ሰነዱ ከተቋማችን ገንዘብ ያዥ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት እቃ ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በምዕ/ጎጃም ዞን ገ/ኢ/ል መምሪያ ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ምዕ/ጎጃም ዞን ገ/ኢ/ትብ/ መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ባሉት የሥራ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በምዕ/ጎጃም ዞን ገ/ኢ/ት/መምሪያ በ3፡30 ታሽጉ በ4፡00 ይከፈታል እለቱ ቅዳሜና እሁድ ወይም ህዝባዊ የበዓል ቀን ከሆኑ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ አቅራቢ የውል ማስከበሪያ በሲፒኦ አስር በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ምዕ/ጎጃም ዞን ገ/ኢ/ትብ መምሪያ ማስያዝና ዕቃዎችን ምዕራብ ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ ንብረት ክፍሎች የማጓጓዣ ወጭ ችሎ ማስረከብ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ ሃያ በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘም ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በማስታወቂያው ላይ ያልተገለፁ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ምዕራብ ጐጃም ዞን ገንዘብና ኢ/ትብብር መምሪያ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 05 87 75 08 95 በመደወል ማብራሪያ ማግኝት ይችላሉ፡፡
የምዕራብ ጐጃም ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር መምሪያ