የጎንደር አካል ጉዳተኞች ክህሎት ማዕከል በ2018 መደበኛ በጀት አላቂ ዕቃዎች እና ቋሚ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡- ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 ብረታ-ብረት ዕቃዎች፣ ሎት 4 MDFና ጣዉላ፣ ሎት 5 ኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ ሎት 6 የሞባይል አክሰሰሪዎች፣ ሎት 7 ጨርቃ-ጨርቅ፣ የሱፍ ክር፣ የመኪና ክርና አክሰሰሪዎች፣ ሎት 8 የህክምና መድሃኒቶች፣ ሎት 9 ራቨርቲፕስና ሀንድል፣ ሎት 10 የዊልቸር መለዋወጫ ዕቃዎች፣ ሎት 11 ሸቀጣ-ሸቀጥ ዕቃዎች፣ ሎት 12 የፕላስቲክ ዕቃዎች ሎት 13 የህትመት ቀለሞች፣ ሎት 14 የመኪና ጎማ ሎት 15 የእንጨትና የብረታ-ብረት ማሽኖች ጥገና፣ ሎት 16፣ ሎት 17 ኤሌክትሮኒክስ ጥገና፣ ሎት 18 ጥገና፣ ሎት 19 የልብስ ስፌት ጥገና፣ ሎት 20 የሹራብ ማሽንኖች፣ ሎት 21 ኤሌክትሮኒክስ እና ሎት 22 ፈርኒቸር ዕቃዎች አቅርቦት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በታች ለሆኑ ግዥዎች ያለ (ቫት) መወዳዳር ይችላል፡፡
- የጨረታዉ አሸናፊ የሚለየው በሎት ድምር ያቀረበ ነዉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የዋጋውን አንድ በመቶ በዋስትና ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ማዘዣ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ግዥና ፋ/ቡ ቢሮ ቁጥር 10 የማይመለስ ብር 20 (ሃያ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላል፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማዘጋጀት በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የመክፈቻ ቀኑም በመጨረሻ በ15 ተኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ጨረታዉ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በማዕከሉ ግዥ/ፋ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሌላ ሰዉ ዋጋ ተንተርሰው ዋጋ መስጠት አይችሉም፡፡
- ሙሉ መግለጫዉን (ዝርዝሩን) እና መመሪያዉን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላል፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በማዕከሉ በግንባር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 211 72 33 ወይም 09 18 30 55 87 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- አድራሻችን ጎንደር ከተማ ቂርቆስ ቀበሌ 06 አሽዋ ሜዳ ት/ቤት/ጎን ነው፡፡
- ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የጎንደር አካል ጉዳተኞች ክ/ማዕከል