ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
11

ወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አገልጋሎት የሚውሉ ሎት 1  መድሃኒት፣ ሎት 2 ሬጀንት፣ ሎት 3 የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች፣ ሎት 4 የተሸከርካሪ ጎማና ባትሪ እና ሎት 5 የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች በሙሉ፡-

  1. ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላችሁ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. ንግድ ፈቃድና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ብር ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  3. የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ከጨረታ ሰነዱና ከታሸገው ፖስታ ላይ የድርጅት ማህተም ተነባቢ በሆነ መልኩ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡
  5. ተጫራቾች ያሸነፉበት የእቃ ዋጋ ድምር ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ 3 በመቶ ተቀንሶ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡ መ/ቤቱ ቫት በመመሪያው መሰረት ይሰበስባል፡፡
  6. ተጫራቾች የሞሉትን የዋጋ አንድ በመቶ በጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወይም ከተፈቀደላቸው ባንክ በተመሰከረለት (ሲፒኦ) በማሲያዝ ከፖስታው ውስጥ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱን በወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተነገራችው በኋላ ማሻሻያ ማድረግ እና ከጨረታ እራስን ማግለል አይቻልም፡፡
  9. የጨረታ ሰነድን ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  10. ተጫራቾች የአማራ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ያወጣውን ግዥ አፈጻጸም መመሪያ አዋጅ ቁጥር 1/2003 እና ተሻሽለው ለወጡ መመሪያዎችና አዋጆች ተገዥ መሆን ይገባቸዋል፡፡
  11. የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከጥቅምት 24/2018 ዓ.ም እስከ ህዳር 14/2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት ተከታታይ ለ21 ቀናት በወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
  12. የጨረታ ሳጥኑ በህዳር 14/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ የጨረታ ሳጥኑ በዚህ ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመመሪያው መሰረት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  13. ተጫራቾች ጨረታ በሚከፈትበት ወቅት ባይገኙም በመመሪያው መሰረት ይከፈታል፡፡
  14. መ/ቤቱም የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. የጨረታ መክፍቻ ቀን በዓል ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ይተላለፋል፡፡
  16. አሸናፊው ማሸነፉ ተነግሮት ውል ከወሰደ በኋላ ሆስፒታሉ በሚያዘው መሰረት ገዝቶ ማቅረብ አለበት፡፡
  17. አሸናፊው ድርጅት ውለታ ከወስደበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 30/2018 ዓ.ም ድረስ ሲታዘዝ ማቅረብ አለበት፡፡
  18. የተጠቀስውን እቃ በጨረታ አሸናፊው ወጭውን ችሎ የሚቀርብ ይሆናል፡፡
  19. ከሎት 1፣ 2 እና ሎት 3 ውጭ ያለው ውድድሩ በሎት ድምር ነው፡፡
  1. ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስራ ሂደቱ ስልክ 033 331 01 72 እና  033 331 02 52 ደወሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here