ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
56

የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል በሥሩ ለሚገኙ የሥራ ክፍሎች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1.የጽ/መሳሪያ፣ሎት 2.የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን፣ ሎት 3 የጽዳት እቃዎችን፣ ሎት 4 የፈርኒቸር እቃዎችን፣ ሎት 5 የሰራተኛ ድንብ ልብስ፣ ሎት 6 የኤሌክትሪክና የግንባታ እቃዎችን፣ ሎት 7 የመኪና ጎማ እና ሎት 8 የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ውል ይዞ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል ዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ በመምጣት ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 በመቁረጥ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በ 2 ፖስታ በማሸግ ዋናና ቅጅ በማለትና በማሸግ ሙሉ ስም ፣የድርጅቱ ማህተም፣ አድራሻውን ከፖስታው ላይ በመፃፍ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመ/ቤታችን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባችዋል ፤ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ህዳር 1/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ጨረታው በ16ኛው ማለትም ህዳር 16/2018 ዓ.ም ጠዋት 3፡30  ታሽጎ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡
  9. የሚገዙ ዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  10. የጨረታ ሰነዱ ሥርዝ ድልዝ ወይም በፍሉድ የተስተካከለ ከሆነ ሰነዱ ተቀባይነት የለውም ወይም መፈረም አለበት፡፡
  11. አሸናፊው በውሉ መሰረትና በወጣው ስፔሲፊኬሽን  በባለሙያ ተረጋግጦ የሚያስረክብ ይሆናል፡፡
  12. ተጫራቾቹ ከዚህ በፊት በአገልግሎት አሰጣጥ ቅሬታ ያልቀረበበት መሆን አለበት፡፡
  13. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይካሄዳል፤ ጨረታው ሲከፈት ያልተገኙ ተጫራቾች በዕለቱ ለሚተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  14. ጨረታ የሚከፈትበት ቀን ብሄራዊ በዓል ከሆነ ለሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  15. መስሪያ ቤቱ አሸናፊው ድርጅት ላይ ከተጠቀሱት ዕቃዎች ብዛት ላይ 20 በመቶ ጨምሮ ወይም ቀንሶ የማሰራት  መብቱ እንደተጠበቀ ነው፡፡
  16. መ/ቤቱ አሽናፊውን የሚለየው በጥቅል ድምር /በሎት/ ዋጋ ይሆናል፤ በመሆኑም ተጫራቾች ሁሉም በጨረታው የተቀመጡትን ዝርዝር  ዋጋ ሙሉ ለሙሉ በጥንቃቄ መሙላት ይጠበቅባችዋል፡፡
  17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  18. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 22 05 04 /09 18 21 06 28 /09 23 22 10 87 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here