በሰሜን ጎንደር ዞን የዳባት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለዳባት ወረዳ ለሁሉም መኪናዎች ዓመታዊ የመኪና መለዋወጫ ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች ሰነድ ግዝታቹሁ መወደዳደር ትችላላችሁ፡፡
- ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑ ግብር የከፈሉ እና 2018 የዘመኑን የንግድ ፈቃዳቸውን ያደሱ የ2017 ዓ.ም የታደሰዉ እስከ ታህሳስ 30/2018 የሚያገለግል መሆኑ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ) ያላቸው፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ የሆኑ፡፡
- በዘርፉ ፈቃድ ያላቸው ማለትም የመኪና መለዋወጫ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- ጨረታው ሲሞላ ሥርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ በመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ዋና እና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዳ/ወ/ግ/ፋ/ን/አስ/ድጋፊ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 23 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ብር ወይም ዋጋ 3 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና መስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ዋና እና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ አጠቃሎ በማሸግ ዳ/ወ/ግ/ፋ/ን/አስ/ድጋፍ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 23 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በተከታታይ 15 ቀናት ከህዳር 03/2018 ዓ.ም እስከ ህዳር 22/2018 ዓ.ም ድረስ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዳ/ወ/ግ/ፋ/ን/አስ/ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 23 በቀን ህዳር 23/2018 ዓ.ም በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ዳ/ወ/ግ/ፋ/ን/እስ/ ድጋፍ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 23 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 113 02 05 ወይም 058 113 04 10 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታው መክፈቻ ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀናት ይከፈታል፡፡
የዳባት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

