የመቀጠዋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለመቀጠዋ ወረዳ መንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤት ሎት ከአጃ፣ አጊሳ እና ሰረቁርና ያለው 7.5 ኪሎ ሜትር የመንገድ ጥገና የማሽነሪ ኪራይ እንዲሁም ሎት 2 ለመቀጠዋ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ለአጃ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመንግስት መደበኛ በጀት አንድ ብሎክ ባለ 04 የመማሪያ ክፍል በመንግስት መደበኛ በጀት በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ለሁሉም ሎቶች (የቫት) ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ ለማሽነሪ ኪራይ የባለቤትነት ሊብሬ መታወቂያ ያለዉ እና ከደረጃ 6 በላይ የሆነ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣ ለአጃ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ ከደረጃ 7 በላይ የሆነ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሠጥ እንደተጫራቹ ምርጫ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆኖ የጠቅላላ ግዥውን ግምታዊ ዋጋ መሠረት በማድረግ አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ የገንዘብ መጠን ተወስኖ በጨረታ ጥሪው እና ሰነዱ ውስጥ መገለፅ ይኖርበታል፡፡ ይህም በመቀጠዋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም ገቢ የሆነበትን የገቢ ደረሰኝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
- ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታ ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበትየመጨረሻቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 20 ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የሚከተሉትን ተግባራት ባለመፈፀሙ ምንያት ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሙሉ በግዥ ፈጻሚው አካል ሊወረስበት ይችላል፡፡
- በጨረታ ሠነዱ የተገለፀው የመጫረቻ ሠነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ጊዜ ካለፈ በኋላ ተጫራቹ ራሱን ከጨረታው ካገለለ፣
- በጨረታው ውድድር አሸናፊ በመሆኑ የውል ማስከበሪያ እንዲያስዝ እና ውል እንዲፈረም ተጠይቆ የውል ማስከበሪያውን ለማስያዝ ፈቃደኛ ካልሆነ፣
- የጨረታው አሸናፊ በጨረታ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከአምስት የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታ አሸናፊው የውል ማስከበሪያ በዚህ ውስጥ በተካተቱ የዋስትና ዓይነቶች የሞሉን ዋጋ 10 በመቶ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች (ሲፒኦ) ወይም በገንዘብ ያዥ መቀጠዋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመሂ 1 በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- በግዥው አፈጻጸም ላይ አቤቱታ ቀርቦ በማጣራት ላይ ካልሆነ በስተቀር አሸፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ተገቢውን የውል ማስከበሪያ ያላሳዘ እና ውል ያልፈጸመ እንደሆነ ግዥ ፈፃሚው አካል የጨረታ ማስከበሪያ የመውረስ መብት አለው፡፡
- ለጨረታ ማስከበሪያ እና ለውል ማስከበሪያ የመድን ዋስትና አገልግሎት የማንቀበል መሆኑን ይታወቅ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን ሙሉ በሙሉ ካልሞሉ እና ሥርዝ ድልዝ ካለዉ ከጨረታ ዉጪ ይሆናሉ፡፡
- ቅድሚያ ክፍያ ወይም 30 በመቶ የማንከፍል (የማንሰጥ) መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ከአሸናፊው የሚቀርበው የውል ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ ውሉ ከሚጠናቀቅበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 30 ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡
- ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በጥቅል ድምር ሆኖ ዝቅተኛ ዋጋ የሞላ አሸናፊ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ የሠነድ ሽያጭ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን ገዝቶ፣ የገዛበትን ሠነድ ኮፒ ማያያዝ ይኖርበታል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዱን ያልገዛ እና የገዛበትን ሠነድ ኮፒ ያልያስያዘ ተወዳዳሪ ከውድድሩ ውጭ እንደሚሆን አውቆ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች (ህጋዊ ወሎቻቸው) ቢገኙም ባይገኙም ጨረታዉ በጋዜጣ በወጣ በ22ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሽገ ፖስታ ውስጥ አድርጎ ኦርጅናል እና ኮፒውን መቀጠዋ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት/ግዥና ንብ/አስ/ ቡድን ዞን ግብርና መምሪያ ጊዜዊ ቢሮ ማቅረብ አለበት፡፡
- እኩል የወጡት ተጫራቾች መሆናቸው ሲረጋገጥ ይኸው ተገልጾላቸው መጀመሪያ በጨረታ ሠነዱ ላይ በተገለጹት መስፈርቶች መሠረት የመጨረሻ የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን እንዲያቀርቡ የሚጠየቅ መሆኑን እና እኩል የወጡት ተጫራቾች ያቀረቡት የመጨረሻ መወዳደሪያ ሀሳብ ተገምግሞ የተሻለ ሀሳብ ያቀረበው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ተደርጎ ይመረጣል፡፡በመጨረሻው ውድድር እኩል ከወጡት ተጫራቾች መካከል ሴቶች ካሉ ቅድሚያ ለሴቶች ይሠጣል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ በሚሞሉበት ሰነድ ላይ ሙሉ ስም ፊርማና የድርጅቱ ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
- ስለጨረታዉ አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማየት ይችላሉ፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ዞን ግብርና መምሪያ ጊዜያዊ ቢሮ በመምጣት መቀጠዋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የመቀጠዋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

