ቁጥር 09/2018
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) ሎት1. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ፣ሎት2. የድምጽ አይዲ ሙዚቃዎችን ፈቃድ ያለቸዉ በግልጽ ጨረታ ዘዴ ተጯራቾችን አወዳድሮ አሸናፊዉን በመለየት መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፍኬት ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት ጠቅላላ ድምር ዋጋ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሎት1 እና ሎት2 በተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ 500 (አምስት መቶ) ብር በመግዛት አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 106 መዉሰድ ይቻላል፡፡ የቴክኒክ እና የፋይናስ ሰነዶችን ለየብቻ በመሙላት ሰነዶችን በሁለት ኮፒ በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት ለዚህ ሲባል በተዘጋጀዉ የጨረታ ሣጥን በ16ኛዉ ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸዉ ፡፡ በቴክኒክ ምዘና 70 እና በላይ ነጥብ ያመጡ ድርጅቶች ወደ ፋይናንስ ዉድድር የሚቀርቡ ይሆናል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ይዘጋና በእለቱ ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥና ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተመሰከረለት ቼክ ወይም ስፒኦ ፣በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት በ16ኛው ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል፡፡
- ቢሮው ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የሚፈለጉትን የኤሌክትሮኒክስ፣ የአይዲ ሙዚቃ ዓይነት፣ ብዛትና ስፔስፍኬሽን እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- የጨረታ ሰነዱን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቀበሌ 13 አየር መንገድ ከሚወስደዉ አስፓልት ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ ባለዉ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 ድረስ በመምጣት መግዛት ይቻላል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 97 35 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን
ባህር ዳር

