ግልጽ  ጨረታ ማስታወቂያ

0
11

በዋድላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ማቴሪያሎችን በድምር (ሎት) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማጫረት ይፈልጋል፡፡ ሎት 1. ጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2. ጽዳት እቃ፣ ሎት 3 ህትመት፣ ሎት 4. ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 5 ደንብ ልብስ በየ ሥራ ዘርፋቸው ተወዳዳሪዎችን አወዳድሮ ከአሸናፊዎቹ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ እና በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) የተሰጣቸው፡፡
  4. ማንኛውንም የሚጠየቁትን መረጃ ማሟላት የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸው ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆኑ (የቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማስታወቂያ ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በዋድላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድረስ በመምጣት ለእያንዳንዱ አይተም ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ይህ ግልጽ ጨረታ በ16 ተኛው ቀን ኦርጅናሉን በማስገባት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ የጨረታ ሰነዱ ታሽጎ በዚሁ እለት 5፡00 ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 በግልጽ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች በጨረታ ሂደቱ በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራቾች በሚሞላው ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ ወይም አሻሚ የሆነ ዋጋ ማቅረብ እና ያልተሟላ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  10. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ስምና ፊርማቸውን እንዲሁም የድርጅቱን ማህተም በማድረግ የገዙትን ሙሉ ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  11. የጨረታ ማስከበሪያ 2 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ (በሲፒኦ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ሲገለጽ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ (ሲፒኦ) በማስያዝ ውል መፈጽም ይኖርባቸዋል፡፡ ሥራው ከተጠናቀቀ እና ክፍያ ከተፈጸመ በኋላ ለተጨማሪ 30 ቀን ፀንቶ ይቆያለ፡፡
  13. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ስለጨረታው ማብራሪያ ከስፈለገ በስልክ ቁጥር 09 18 49 45 61 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ ፡- ሁሉም ተጫራች 15 በመቶ (ቫት ) ተመዝጋቢ መሆን አለበት፤ አሸናፊው እቃውን  በራሱ ወጭ ሆስፒታል ድረስ ማምጣት አለበት፡፡

የዋድላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here