ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
137

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርኘራይዝ በሀገር ውስጥ ገበያ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የተለያዩ ንፁህ አኩሪአተር እና ወንዴናአማላ በቆሎ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡   ስለዚህ መስፈርቶችን የምታሟሉ በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ፤ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፤ ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ የተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት /ቲን/ ፎቶ ኮፒ በማድረግ የማይመለስ 50.00/ሀምሳ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ባሕር ዳር አለ በጅምላ (ጅንአድ) ግቢ ውስጥ በሚገኘው የኢንተርኘራይዙ መሥሪያ ቤት ገንዘብ ያዥ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ላቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. የጨረታው አሸናፊ ድርጅቶች የአሸነፉትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከኢንተርፕራይዙ ጋር ዝርዝር ውል መፈራረም ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በተገለፀው መሠረት የጨረታውን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ለአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርኘራይዝ በማለት የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች ትክክለኛ ስምና አድራሻ በመጻፍ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ በሥራ ሰዓት በኢንተርኘራይዙ ዋና መሥሪያ ቤት /ባሕር ዳር/ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. ጨረታው በጋዜጣ በወጣበት በአስረኛው የሥራ ቀን 8፡00 ተዘግቶ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓላት ቀን ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሸጋገራል፡፡
  6. ድርጅቶች ዋጋ ከሞሉበት ሰንጠረዥ ላይ እርጥብ ማህተም ወይም ፊርማ ማድረግ አለባቸው፡፡
  7. የተለያዩ ንፁህ ዘሮችና የምግብ እህሎች በተመለከተ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ናቸው፡፡
  8. ያገለገሉ ጆንያዎችና ብጣሪን በተመለከተ ንግድ ፈቃድ እንዲያቀርብ አይገደድም፡፡
  9. ግዠውን በተመለከተ ባሕር ዳር ዋናው መሥሪያ ቤት መጋዘን መድሀኒዓለም አካባቢ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ሌሎች ሰብሎችን በተመለከተ ባሕር ዳር፣ ኮምቦልቻ፣ እንጅባራ ፣ ብር ሸለቆ እና ደብረ ብርሀን የሚገኙ ሲሆን ዝርዝሩን ከጨረታ ሰነዱ ይመልከቱ፡፡
  10. ኢንተርኘራይዙ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ኢንተርኘራይዙ ለግዥም ሆነ ለሽያጭ ከተጠየቀው ውስጥ እንደአስፈላጊነቱ መጠን አስከ 50 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  12. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ኢንተርፕራይዙ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 226 60 02 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 84 15/ 09 18 01 69 35 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርኘራይዝ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here