በደቡብ ጎንደር ዞን ለደብረታቦር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የህንፃ እድሳት ለማስጠገን ፈቃዳቸው ከደረጃ 1-4 ያሉ ተቋራጭ እና ልዩ የሥራ ተቋራጭ እንዲሁም በ2017 ዓ/ም ግንባታ ገንብተው መልካም ሥራ አፈፃፀም ካላቸው ተቋራጮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በዝቅተኛ ዋጋ ከሞሉ ተወዳዳሪዎች ማሰራትና ማስጠገን ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ማስረጃ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፍያ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚፈለግባቸውን ማስረጃዎች ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር በማቅረብ ኮፒውን ከተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ከኮሌጁ ግዥ ባለሙያ ቢሮ ፊት ለፊት ከሚገኝው ሳጥን ማስገባት ይኖረባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጠቅላላ ድምር ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም (ቫት) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የሚስራውን የስራ አይነት (ስፔስፊኬሽኑን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ኮሌጁ ቫት ከብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ እና ዊዝሆልዲንግ ታክስ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በላይ ከሆነ ኮሌጁ ግብር ሰብሳቢ ስለሆነ ቀንሶ ያስቀራል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ከኮለጁ ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 7 መክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋሰትና (ቢድ ቦንድ) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት (በሲፒኦ) በጥሬ ገንዘብ ከሚሞላው ጠቅላላ ዋጋ ብር አንድ በመቶ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን ዋጋ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ ላይ ስሙን እና አድራሸውን በመፃፍ ደብረ ታቦር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በግዥ ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀዉ ሳጥን ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ከወጣበት በሥራ ቀናት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታዉ የሚከፈትበት በ22ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ በ4፡15 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም ጨረታዉ ይከፈታል እለቱ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ ካለው ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡ ፓራፍ (ልዩ ፊርማ ቢያደርጉም) ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ተጫራቹ የሚያቀርበዉን ደረሰኝ በራሱ ስም የታተመና ተከታታይ የደረሰኝ ቁጥር ያለዉ መሆን አለበት
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 05 99 በመደወል ወይም ከኮሌጁ የግዥ ባለሙያ ቢሮ ቁጥር 1 በአካል በመገኘት መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ደብረታቦር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

