ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
52

በሰሜን ወሎ መስተዳደር ዞን መምሪያ የዳውንት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብ/አስ/ር ቡድን ለኩርባ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት  ለቅድመ መደበኛ የመማሪያ ክፍል ግንባታ በመልሶ ማቋቋም ፈንድ በጀት ግዥ እንዲፈጸምላቸዉ ባሳወቁን መሰረት ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውን በጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አዉጥቶ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግንባታዉን ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ  የዳውንት ወረዳ ገ/ጽ/ቤት የግዥናን ንብ/አስ/ቡድን  የተዘረዘሩትን  መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)፣ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ኦርጅናልና ኮፒ መረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆኑ የተጨማሪ ሴት ታስክ (ቫት) የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የሚሙሉትም ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 100,000 (አንድ መቶ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሥሪያ ቤቱ ህገዊ ደረሰኝ ተቆርጦ ከሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
  4. በማንኛውም ግዥ ለግንባታዉ ከብር 10,000 (አስር ሽህ ብር በላይ) እና ለአገልግሎት ግዥ ከብር 3,000 (ሶስት ሽህ ብር) በላይ 3 በመቶ የቅድመ ግብር ተቀንሶ ገቢ ይደረጋል፡፡
  5. ተጫራቾች ከላይ ለተገለፁትን ግንባታዎች የጨረታ ሰነድ ቢሮ ቁጥር 15 እራሳቸው ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፈቃዳቸውን በማሳየት ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን እና የንግድ ፈቃድ መረጃቸውን ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻው በፖስታ  በጥንቃቄ  በማሸግ  የጨረታው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት  የሚቆይ ሲሆን  እስከ 16ኛው ቀን 3፡30 ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ዳ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 15 በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት  ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ  4፡00 ላይ ማለትም በጥር 19/2018 ዓ.ም ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት አያስተጓጉለውም፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ለቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው የሥራ ዝርዝር በመገለጫው መሰረት በሰነዱ በእያንዳነዱ በግልጽ ዋጋውን መሙላት እና የድርጅታቸውን አድራሻ፣ ስም፣ ማህተምና ፊርማ ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች በሞሉት በነጠላ ዋጋ እና በጠቅላላ ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውጪ እንደሚሆኑ ማወቅ አለባቸው፡፡
  10. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ካሉ በክልሉ የግዥ አዋጅ 179/2003 እና በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ከጨረታ ውጭ እንደሚደረጉ፣ ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ ውርስ እንደሚደረግ እና በተመሳሳይ ሌላ ጨረታ እንደይሳተፉ ይደረጋል፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ውድድሩ በ ጠቅላላ ድምር ዋጋ መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል፡
  12. ተጫራቾች በጨረታው ውጤት ቅር ከተሰኙ የጨረታ ውጤቱ በማስታወቂያ ቦርድ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅሬታቸውን በየደረጃው ላለ የፋይናንስ ተቋማት ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቅ ይችላሉ፡፡
  14. ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ ቢፈልጉ ቢሮ ቁጥር 15 ደረስ በመምጣት በስልክ ቁጥር 033 241 91 37 በመደወል  መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የዳውንት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here