ቁጥር 12/2018
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) የስቱዲዮ ኢንቴረር ስራ ሎት1. ስቱዲዮ ሀ እና ስቱዲዮ ለ የእንግዳ ማረፊያ ክፍል፤ ሎት2. ኀብር ስቱዲዮ እና ሎት3. መዋቢያ ክፍል እና ዳይሬክተር ቢሮ ይህንን ስራ ለማሰራት ለሎት 1 ደረጃ 6 እና ከዛ በላይ ሆኖ ደረጃ 8 የህንፃ ማጠናቀቅ ስራ ወይም የማስዋብ ፈቃድ ያላቸዉ፤ ሎት2 እና ሎት3 ደረጃ 8 እና ከዛ በላይ ሆኖ የህንፃ ማጠናቀቅ ማስዋብ ስራ ፈቃድ ያላቸውን ተቋራጮች፤ ሎት4. የተለያዩ የፈርኒቸር እቃዎችና አኳስቲክ ስራ፤ ሎት 5 የድምፅ የአይዲ ሙዚቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊዉን በመለየት ማሰራትና መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፡የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡ የከተማ ልማት የብቃት የምስክር ወረቀት፡የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፍኬት፣ ማስረጃውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት ጠቅላላ ድምር ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ እና ከዚያ በላይ ከሆኑ የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሎት1 ፣ ሎት2 እና ሎት3 በተከታታይ 21 (ሃያ አንድ) ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ እንዲሁም ሎት4 እና ሎት 5. ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀን ብር 500 (አምስት መቶ) በመግዛት አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 106 መዉሰድ ይቻላል፡፡ ሎት 1፣ ሎት 2 እና ሎት3 የፋይናንስ ኦርጂናልና ኮፒ ሰነዶችን በሁለት ኮፒ በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት ለዚህ ሲባል በተዘጋጀዉ የጨረታ ሣጥን በ22ኛዉ ቀን 4፡00 ድረስ እንዲሁም ሎት4 የፋይናንስ ኦርጂናልና ኮፒ ሰነዶችን በሁለት ኮፒ በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት ለዚህ ሲባል በተዘጋጀዉ የጨረታ ሣጥን በ16ኛዉ ቀን 4፡00 ድረስ በተጨማሪም ሎት5 ቴክኒካልና የፋይናንስ ኦርጂናልና ኮፒ ሰነዶችን በሁለት ኮፒ በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት ለዚህ ሲባል በተዘጋጀዉ የጨረታ ሣጥን በ16ኛዉ ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸዉ ፡፡
- ጨረታው ሎት1 ፣ ሎት2 እና ሎት3 በ22ኛዉ ቀን ከቀኑ 4፡00 ይዘጋና በእለቱ ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥና ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ይከፈታል። በተጨማሪም ሎት4 እና ሎት5 በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ይዘጋና በእለቱ ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥና ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተመሰከረለት ቼክ (ስፒኦ) ፣በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ሎት1 ፣ ሎት2 እና ሎት 3 የሚከፈትበት በ22ኛዉ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል፤ እንዲሁም ሎት4 እና ሎት5 በ16ኛው ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል፤ የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል፡፡
- ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የሚፈለጉትን የሎት1፣ የሎት2፣ የሎት 3፣ የሎት4 እና ሎት5 ዓይነት፣ ብዛትና ስፔስፍኬሽን እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- የጨረታ ሰነዱን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቀበሌ 13 አየር መንገድ ከሚወስደዉ አስፓልት ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ ባለዉ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 ድረስ በመምጣት መግዛት ይቻላል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 97 35 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን
ባህር ዳር

