ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
68

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ከብርሸለቆ እርሻ ጣቢያ መነሻዉ የሆነ ንፁህ ለምግብ የሚሆን በቆሎ ብዛቱ 10,000 (አስር ሽህ) ኩንታል ለመሸጥ በደብረ ብርሀን ዘር ማከማቻና ማበጠሪያ ጣቢያ አጥር ግንባታ ለማስገንባት እና የተለያዩ መኪኖች ባለ 60 ወንበር አዉቶብስ፣ባለ 30 ወንበር ኮስትር ሀይብሪድ አዉቶሞቢል ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ፣ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስና የዘመኑን ግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት(ቲን)ፎቶ ኮፒ በማድረግ፤ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር/10/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ጓዳ ማሽ ቀን ጨምሮ  ዘወትር በስራ ሰዓት ባሕር ዳር አለ በጅምላ (ጅንአድ) ግቢ ውስጥ በሚገኘው የኢንተርኘራይዙ መስሪያ ቤት ገንዘብ ያዥ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ላቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. የጨረታው አሸናፊ ድርጅቶች የአሸነፉትን ጠቅላላ ዋጋ 10በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከኢንተርፕራይዙ ጋር ዝርዝር ውል መፈራረም ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ለግንባታዉ የሚጠይቀዉ የሥራ ፈቃድ ደረጃ ስድስት እና ከዚያ በላይ ሲሆን፤ የሙያ ብቃት ማስረጃና የመልካም ሥራ አፈፃፀም ያላቸው፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በተገለፀው መሠረት የጡረታውን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ለአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርኘራይዝ በማለት የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች ትክክለኛ ስምና አድራሻ በመፃፍ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር ተከታታይ የሥራቀናት ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ በሥራ ሰዓት በኢንተርኘራይዙ ዋና መስሪያ ቤት (ባሕር ዳር) ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በአስረኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 6፡30 ይዘጋል፡፡ በዚሁ ቀን 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ጨረታው በሚከፈትበት  ቀን የበዓላት ቀን ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሸጋገራል፡፡
  7. ድርጅቶች ዋጋ ከሞሉበት ሰንጠረዥ ላይ እርጥብ ህማተም ወይም ፊርማ ማድረግ አለባቸው፡፡
  8. የተለያዩ ንፁህ ዘሮችና የምግብ እህሎች በተመለከተ ተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ናቸዉ፡፡
  9. ግዠዉን በተመለከተ ባህር ዳር ዋናዉ መስሪያ ቤት መጋዝን መድሀኒዓለም አካባቢ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ኢንተርኘራይዙ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረክ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ኢንተርኘራይዙ ለግዥም ሆነ ለሽያጭ ከተጠየቀዉ ዉስጥ እንደአስፈላጊነቱ መጠን እስከ 50 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 320 84 15/09 18 01 69 35 መደወል ይቻላል፡፡ እንዲሁም በፋክስ ቁጥር  058 226 60 02 በመላክ ማግኘት ይቻላል፡፡

የአማራ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here