ግልጽ  ጨረታ  ማስታወቂያ

0
17

በማዕከላዊ ጐንደር ዞን የጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ሎት 4 የስፖርት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸዉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በግዥና /ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ባሉት የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሽህ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም ከ60 (ስልሳ) ቀን ያላነሰ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ (ቢድ ቦንድ) እንዲሁም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ በጥሬ ገንዘብ ካስያዙ ከኮሌጁ ገንዘብ ቤት ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ኮፒ ከፖስታዉ ዉስጥ ማስገባት  ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጠ/ጤ/ሣ/ኮሌጅ በግዥና /ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ1 0፡00 ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ስዓት ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ጨረታዉ በዚህ ዕለት ከቀኑ 10፡00 ታሽጎ በ16ኛዉ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  8. ዕቃው መለያ ዝርዝር (ሰፔስፊኬሸን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ዉድድሩ የሚካሄደው በሎት ምድብ ነው፡፡
  9. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ ኮሌጁ በሚያቀርበዉ ናሙና መሰረት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  10. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. በጨረታው ላይ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ 058 448 02 34 ደውለው መጠየቅ ወይም ጠ/ጤ/ሣ/ኮሌጅ በግዥና /ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 በመምጣት መረጃውን ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here