ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
7

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በሰቆጣ ከተማ ዋቢ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒዬን ኃ/የተወሰነ ከመትሃራ ስኳር ፋብሪካ ከወንጂ/ዴራ ስኳር ፋብሪካ ከከሰም ስኳር ፋብሪካ፣ ከወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ከአዲስ አበባ እና ከግልገል በለስ ስኳር ፋብሪካ ወደ ሰቆጣ፤ ዋቢ ዩኒዬን መጋዘን ማሾና ሰሊጥ ከሰቆጣ ወደ ኮምቦልቻ ለማድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት ግልጽ ጨረታ በማወዳደር ስኳርና ዘይት ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡

  1. በ2018 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ከሚጓጓዘው የትራንስፖርት (የጭነት) አገልግሎትና የትራንስፖረት ፈቃድ ጋር የተዛመደ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት (Tax payer identification Number) እንዲሁም ሌሎች ለጨረታው የሚጠቅሙ ማስረጃዎችን የተገናዘበ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚገዛውን የትራንስፖርት አገልግሎትና የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ የጨረታ ሰነድ ሰቆጣ ከተማ ወይብላ ማርያም አጠገብ ከሚገኘው ዋቢ ዩኒዬን ቢሮ ቁጥር 1 በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በሌላ ዋጋ ላይ ተመስርተው መወዳደር የማይቻሉ ሲሆን የጨረታ ማስከበሪ ዋስትናው አሸናፊ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 5 ቀናት እንዲሁም የውል ማስከበሪያ ዋስትናው ውል ከተፈጸመበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 30 ቀናት ፀንቶ ሊቆይ የሚችል መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በተፈቀደላቸው በታወቁ ባንኮች ዋስትና (ሲፒኦ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ዋቢ ዩኒዬን ገቢ በማድረግ/ዋናውን የገቢ ደረሰኝ ከማወዳደሪያ ሃሳብ ጋር አብሮ ማስገባት ይኖርባቸው በጨረታ ሰነዱ ከተቀመጠው ዝርዝር መግለጫ ውጭ መጨመርም ሆነ መቀነስ አይፈቀድም፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ 15 ተከታታይ ቀናት ሰነዱን በመግዛት የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሰቆጣ ከተማ ወይብላ ማሪያም በስተጀርባ ከሚገኘው ዋቢ ሁለገብ /የገ/ህ/ስ/ማ/ኃላፊነቱ የተወሰነ ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በ16ኛ ቀን 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱ የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ዋቢ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማ ሃላፊነቱ የተወሰነ ጨረታው ከወጣበት ቀን ለተከታታይ 15 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ወጥቶ ቆይቶ በ16 ተኛው ቀን ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪል) በተገኙበት ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ጨረታው ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ሀሳባቸውን ለማሻሻል ወይም ከጨረታው ለመውጣት የፈለጉ እንደሆነ የጨረታ ማወዳደሪያ ሃሳብ ለማቅረብ ከተሰጣቸው 3 ቀን በፊት በጽሁፍ ሊያሳውቁ ይገባል፡፡

ዋቢ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒዬን ኃ/የተወሰነ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here