የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለስልጣን በበጀት ዓመቱ ከሚያሠራቸው ፕሮጀክቶች መካከል 1ኛ. የአስፓልት ጥገና ሥራ ከዋተር ፍሮንት ሆቴል ፊትለፊት እና ከአጅፕ እስከ እልልታ ሆቴል በስተግራ አቅጣጫ ያለውን የአስፓልት ጥገና ማሠራት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡
- ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ደረጃ 2 የሆኑ፡፡
- የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
- ከላይ የተጠቀሰውን ፕሮጀክት ለማሠራት አስፈላጊውን ሁሉ የሰው ሃይል፣ የማቴሪያል እንዲሁም የመሳሪያ አቅርቦቶችን የሚያሳይ በስማቸው የታሸገ የፋይናንሽያል እና የቴክኒካል የመወዳደሪያ ሃሳቦችን ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ሕጋዊ ተጫራች ባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን የግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 ስልክ ቁጥር 058 320 18 78/058 320 32 46፣ የማይመለስ 1‚500.00 /አንድ ሽህ አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የተጫራቹንና የኘሮጀክቱን ስም በግልፅ ተቀባይነት ባለው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልመሰረተ የባንክ ዋስትና ጨረታ ዝርዝር መረጃ ሰንጠረዥ የተጫራቾች መመሪያ ተ.መ1 ላይ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች መመሪያ በማንበብ ሙሉ ፈቃደኛ እንዲሆኑ ይመከራሉ፡፡
- ኘሮጀክቶች የሚጠናቀቁበት ቀን በክፍል 8 አንቀጽ አ.ው.ሁ1 ላይ በተገለጸው ቀን መሰረት ይሆናል፡፡
- ሁሉም የቅድመ ማጣሪያ/ቴክኒካል/ እና ጨረታ ዋጋ/ፋይናንሻል/ ሰነዶች በተለያዩ ኢንቨሎፓች ማህተም በማድረግ መታሸግ ይኖርባቸዋል፡፡ (አንድ ኦርጅናል አንድ ኮፒ) መሆን አለበት፡፡
- ጨረታው ሁለት የግምገማ ሂደቶች ይኖሩታል፤ የመጀመሪያው ሂደት/ደረጃ የቴክኒካል ሰነዶች ግምገማ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ቴክኒካል ግምገማውን ካለፉት ተጫራቾች ውስጥ የአብክመ ገንዘብ ቢሮ በቁጥር አብክመ ገ/ቢ/ኮቢ-01/02 በቀን 15/09/2014ዓም በተሸሻለው መመሪያ መሰረት የጨረታ ዋጋ ያቀረበውን ተጫራች መምረጥ ይሆናል፡፡ ለበለጠ መረጃ መመሪያውን በደንብ ያንብቡት፡፡
- የታሸጉ የቅድመ ማጣሪያና የጨረታ ዋጋ ሰነዶች የሚቀርቡት ለመንገዶች ባለስልጣን የግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት ሆኖ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ቀን ከ2፡30 እስከ 11፡00 ታሽጎ ይዘጋል፤ ጨረታው በይፋ የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 3፡30 ላይ በግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 7 ውስጥ ይሆናል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ከሥራ ቀናት ውጭ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ማንኛውንም ተጨማሪ መረጃ ከባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን ስ.ቁ 058 320 18 78/058 320 32 46 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- በባሕር ዳር ከተማ ውስጥ በባለፈው ዓመት ፕሮጀክት ጀምሮ ያቋረጠ ወይም በተሰጠው ውል መሰረት ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ያሉት ተጫራች መሳተፍ አይችልም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ከሥራ ዝርዝሩ ውስጥ ወይም ከዚህ በላይ ለተዘረዘሩ የሥራ አይነቶች የነጠላ ዋጋ ሳይሞላ ቢቀር ያለ ክፍያ ሥራውን እንዲሠራ ይገደዳል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ከማስገባቱ በፊት የሳይት ጉብኝት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ ስለዚህ አሠሪ መስሪያ ቤቱ ከሳይቱ ሁኔታ ጋር የተያያዙ ቅሬታዎችን አይቀበልም፡፡ ተጫራቾች በሚሞሉት ሰነድ ላይ የሚፈጠር ስርዝ ድልዝ ከውድድር ውጭ የሚያደርግ ይሆናል፡፡ ለበለጠ መረጃ ከሰነዱ ጋር የተያያዙ ሰነዶችን ይመልከቱ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ከቴክኒካል ሰነዱ ውስጥ ከጠቅላላ ውሉ 10 በመቶ ያህሉን ለሥራ እድል ፈጠራ ለማዋል መስማማቱን የሚገልፅ ሕጋዊ ማረጋገጫ ደብዳቤ አብሮ ማያያዝ አለበት፡፡ ካልሆነ ግን ‹‹በጥቃቅን አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ለተደራጁ ወጣቶች የሥራ እድል አማራጮችን ለማስፋትና ለማበረታታት የተዘጋጀ መመሪያ ቁጥር 27/2009 ዓ/ም›› መሰረት ተጫራቹ ውድቅ የሚደረግ ይሆናል፡፡
- የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለስልጣን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡