ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
137

የባሕር ዳር ከተማ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ለ2016 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ HDPE PIPE በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 210 የጨረታ ሰነዱ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር ) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት ኦርጅናል እና ኮፒ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በዋናው ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የቴክኒካል ማወዳደሪያ ሰነድ እና የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነዳቸውን በተለያየ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሁለት በመቶ ብቻ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /unConditional Bank Garanty/ ከኦርጅናል ወይም ከቴክኒካል ጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
  8. ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ክፍት ሆኖ በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 2ኛ ፎቅ ግ/ንብ/አስ/ንዑ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 202 ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በ8፡30 ይከፈታል፡፡
  9. አሸናፊዎች አሸናፊነታቸው ከተለየበት ቀን ጀምሮ ከ 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ጽ/ቤቱ ድረስ በመቅረብ 10 በመቶ  የውል ማስከበሪያ  በማስያዝ እና ውል በመፈፀም ባ/ዳር ከተማ ውሃ አገ/ጽ/ቤት በመቅረብ ወደ ሥራ መግባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 32ዐ 5ዐ 79  ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የባሕር ዳር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here