ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
124

የአብክመ ፍትህ ቢሮ ለ2016 ዓ.ም  ሎት 1. የጽህፈት መሣሪያ እና ሎት 2. የዋይፋይ

እቃዎች ግዥ  የሚከተሉትን መስፈርቶች ከሚያሟሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. የግዥው መጠን ከብር 200,000.00/ሁለት መቶ ሽህ / በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገበ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ.ቁ.1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፤ ነገር ግን ከላይ ከ1-4 የተጠቀሱትን ያላቀረበ ተጫራች ከጫራታው ውጭ ይሆናል፡፡
  4. ተጫራቸች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ብቻ በመክፈል አብክመ ፍትህ ቢሮ ከግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 /የገንዘብ ያዥ ቢሮ/ መግዛት ይቻላል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ የዕቃውን ወይም የአገልግሎቱን ዋጋ ለጽ/መሣሪያ ሎት1. ብር 3,000.ዐዐ/ሶስት ሺህ ብር/ እና የዋይፋይ እቃ ሎት2. ብር 5,000.00/አምስት ሺህ / በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸው ላይ በእያንዳንዱ ገፅ ማህተማቸውንና ፊርማቸውን በማሰፈርና ፖስታውን በሚገባ በማሸግ ለአብክመ ፍትህ ቢሮ ግዥ ባለሙያዎች ቢሮ ቁጥር 04 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ 12/ 9 /2016 እስከ 15ተኛው ቀን 26/9/2016 ዓ/ም ከጠዋቱ  3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አብክመ ፍትህ ቢሮ በመ/ቤቱ ቢሮ 04 በ16ተኛው ቀን በ 27/9/2016ዓ.ም በ3፡30 ተዘግቶ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  8. በሚገዙ የዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  9. በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በመ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582263100/ በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

የአብክመ ፍትህ ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here