የፍ/ሠላም ሆስፒታል ለ2017 ዓ/ም በጀት አመት አወትሶርስ የተደረጉ አገልግሎቶችን ማለትም ሎት 1 አጠቃላይ የግቢዉን የጽዳት ሥራ ሎት 2 የጄኔረተር እና የመኪና ቅባቶች ግዥ ለመፈጸም በዘርፉ ፈቃድ ያአላቸዉ ነጋዴዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለ2017 በጀት አመት ለአንድ ዓመት ዉል በመያዝ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ከዚህ በታች በዝርዝር የቀረቡትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በውድድሩ እንዲሳተፋ ይጋብዛል፡፡
- የታደሰና በዘርፋ ህጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የግብር ከፋይነት መለያ /ቲን/ ሰርተፊኬት ያላቸው ማቅረብ የሚችሉ እና የጽዳት አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚሰራው የሥራ ዝርዝር መግለጫ /እስፔስፊኬሽን/ እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50.00 /ሀምሳ ብር / በመክፍል ግዥ ፋይናስ የስራ ሂድት ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቅናት በአየር ላይ የሚዉል ሲሆን በተጠቀሰዉ ቀን ዉስጥ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የጽዳት ተጫራቾች የሞሉትን የ12 ወር ሂሳብ የጨረታ ማስከበሪያ ሁለት በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ጨረታውን ቢያሸነፋ የውል ማስከበሪያ አስር በመቶ በሲፒኦ የሚያሲዙ ይሆናል፡፡ የጄነኔተር እና የመኪና ቅባት አቅርቦት ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ 5000.00 /አምስት ሺህ ብር/ የዉል ማስከበሪያ 15000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ በሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአማረኛ ቋንቋ ሰርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መሠረት በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም በየገጽ በማድረግና በፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሆሰፒታሉ ግዥ ፋይናስ ደጋፊ የስራ ሂድት ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታዉ በአየር ላይ የሚዉለዉ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ ቀን በዓየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ የሚታሸግ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ጨረታዉ በበኩር ጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛዉ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይናስ ቢሮ ከፍል ከቀኑ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ለመከፈት አይሰተጓጓልም፡፡
- ሰለጨረታው ዝርዝር መረጃ /ማብራሪያ/ ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 775 10 16 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡ መ/ቤቱ ጨረታው
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ በሙሉ የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
የፍኖተ ሠላም ሆስፒታል