በአብክመ የሴቶች ወጣቶች ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እና የባህል ቱሪዝም ቢሮ የጽ/መሳሪያ ፣ የጽዳት ዕቃ ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ፣ ፈርኒቸር ፣የደንብ ልብስና የልብስ ስፌት የእጅ ዋጋ ፣የባነር ህትመት ፣ዓመታዊ የተለያዩ መጽሄት፣ ክብ ማህተም እና የስም እና የስልጣን ቲተር፣ መታወቂያዎች እና የደረት ባጅ እንዲሁም የመኪና ጎማ ከነከለመዳሪው ፣የመኪና ዲኮርና የብስክሌት ጎማ ከነካላማዳሪው ዓመታዊ ግዥ ለቢሮው አገልግሎት የሚውል የ2018 በጀት ዓመታዊ ግዥ በግልፅ ጨረታ አውዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000/ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ
እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ተነባቢና ግልፅ የሆነ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በ 200 /ሁለት መቶ / ብር ከግ/ፋይ/ንብ/አስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 213 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የዕቃው ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይንም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሴ/ወ/ማ/ጉ/ቢሮ በግ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሪት ወይም ቢሮ ቁጥር 213 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 15ኛው ቀን ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋይ/ንብ/አስ ዳይሬክቶሪት ክፍል በቢሮ ቁጥር 213 በ16ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ በዛው ቀን በ8፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 213 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 0582204270 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 58 64 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
አድራሻ ፡- ባ/ዳር ቀበሌ 16 ግብርና ምርምር ቢሮ ፊት ለፊት ይገኛል፡፡
የአብክመ ሴ/ወ/ማ/ጉ/ቢሮ

