የጨረታ ቁጥር:- ግጨ-04/2017
የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ለራሱ ለፕላንና ልማት ቢሮ እንዲሁም በፑል አገልግሎት ለሚሰጣቸው ለትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ባለስልጣን እና ለአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ባለስልጣን የ2018 በጀት ዓመት ሎት1. የፅህፈት መሳሪያዎች ፣ሎት2. የፅዳት ዕቃዎች ሎት3. የፈርኒቸር ዕቃዎች፣ ሎት4. የኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ ዕቃዎች አቅርቦት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ አግባብ ያለው እና የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000/ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ለሚገዙ ዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500/ አምስት መቶ ብር / በመክፈል በአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ቁጥር 223 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒዩ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ሠነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ በሚል ስም ተዘጋጅቶ መቅረብ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የእያንዳንዱን ተቋም በመለየት ለሎት1. (የፅህፈት መሳሪያዎች) ፣ለሎት.2 የፅዳት ዕቃዎች እና ለሎት.3 የፈርኒቸር ዕቃዎች ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዳቸውን ብቻ የዋጋ መወዳደሪያ እንዲሁም ለሎት.4 የኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ ዕቃዎች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በተለያየ ፖስታ ማለትም ቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዳቸውን በአንድ ፖስታ ቴክኒካል መመዘኛ እና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሌላ ፖስታ የዋጋ መወዳደሪያ የሚል ፅሁፍ በመፃፍ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም ከጧቱ 4፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ ኘላንና ልማት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 001 ህዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም ከጧቱ 4፡00 ይታሸግና በዚሁ ቀን ከጧቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የሚመረጠው ለሎት1 እና ለሎት2 በእያንዳንዱ ተቋም በሎት ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ እንዲሁም ለሎት3 እና ለሎት4 በነጠላ ዋጋ ዝቅተኛ ያቀረበ ድርጅት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአብክመ ኘላንና ልማት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 001 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 64 27 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ

