የአብክመ የከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ ለምእራብ ቀጠና አራት ቅ/ጽ/ቤት ለ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ አመታዊ የቢሮዎች፣ የመጸዳጃ ቤትና የግቢ የጽዳት አገልግሎት ፤ለጽዳት አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን ግዥ በመደበኛ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅቶት ጋር ውል በመያዝ ግዥው መፈጸም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- በዘመኑ ግብር የከፋሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብረ ክፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ አመታዊ የቢሮዎች፣የሽንት ቤትና የግቢ የጽዳት አገልግሎት/ለጽዳት አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን/ አይነትና ዝርዝር መግልጫ /ሰፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከቢሮው ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 27/28 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ወይም /የአገልግሎቱ/ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ ብር 390.00 (ሶስት መቶ ዘጠና ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ በቢሮዉ ገንዘብ ያዥ ገቢአድርገው ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆኑ 2 ፖስታዎች ማለትም ዋናና (ኦርጅናል) እና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ከተማ ልማት ቢሮ ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ስለሆነም የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚቻለው እስከ 15ተኛው ቀን 11፡30 ብቻ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ በ16ኛ ቀን በ3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ይከፈታል ቅዳሜ ፣ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 30 ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 50 00 /05822661 80/ በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ዋጋወን ሲሞሉ ያለምንም ስርዝ ድልዝ መሆን ይኖርበታል፡፡ ይህ ካለሆነ ሰነዱ ተቀባይነት አይኖረውም ባጋጣሚ የተሰረዘ ከሆነ የተሞላው ዋጋ ከተሰረዘው ቦታ ባጠገቡ መፈረም አለበት፡፡
የአብክመ የከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ


