ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
16

የግዥ መለያ ቁጥር ፡ አብክመ/ኢቴቢ/ግ/ጨ/ 02 / 2018

በአብክመ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ በግቢው ውስጥ የሚገኘውን ከፍተኛ መጠን ያለውን የህንፃ ፍርስራሽ የፌሮ ብረት በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ሎት 1.የተለያዬ መጠን ያላቸው የህንፃ ፍርስራሽ ፌሮ ብረቶች ሽያጭ ፣ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳፋ ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ. 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የሚሸጠውን የብረት ዓይነትና መጠን በአብክመ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ቅጥር ግቢ ውስጥ (ባህር ዳር – ሙሉአለም የባህል ማዕከል ጎን ) በመምጣት ማየት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች በተቋሙ ዋ/ገንዘብ ያዥ ቢ/ቁ / 02 በመምጣትና የማይመለስ ብር 500 / አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ወይም ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ ) ብር 50,000 (አምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ. ኦ ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች ጨረታው በበኩር ጋዜጣ ከወጣበት ከቀን 24/02/2018 ዓ.ም እስከ 08/03/2018 ዓ.ም ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 20 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው በ 08/03/2018 ዓ.ም ቀን ከቀኑ በ 8፡00 ተዘግቶ በዕለቱ በ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 20 ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰአት ይከፈታል፡፡
  10. የጨረታ መስፈርቶችን አሟልቶ ከፍተኛ የኪሎ ግራም ዋጋ ያቀረበ ተጫራች የጨረታው አሽናፊ ይሆናል ፡፡
  11. ቢሮው የንግድ ፈቃድ አውጥቶና ደረሰኝ አሳትሞ ለንግድ ያልተቋቋመ (የመንግስት መ/ቤት) በመሆኑ በሽያጩ ከሚያገኘው ክፍያ ላይ ማንኛውንም ዓይነት ግብር አይቆረጥበትም ፡፡
  1.  መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  2.  ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፤ ካላደረጉ ከውድድር ውጪ ይሆናሉ ፡፡
  1. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 20 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 68 56 በመደወል ማግኘት ይችላሉ ፡፡

የአብክመ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here