ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
27

የምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት ለዞን መምሪያዎች በመደበኛ በጀት በሎት (ምድብ) የተለያዩ አቅርቦቶች ሁነው ተዛማጅ ወይም ተቀራራቢ ባህሪና ጠቀሜታ ያላቸውን አንድ አይነት የንግድ ወይም የሥራ ፈቃድ ከተሰጣቸው አቅራቢዎች መግዛት የሚፈልግ ሲሆን ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች እንዲሁም ሎት 4 የፈርኒቸር ዕቃዎች ግዥ በጋዜጣ ግልጽ ጨረታ አወዳደሮ ሸናፊውን ለይቶ የኩንትራት ውል በመያዝ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡- ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መጫረት ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ለሆነ ግዥ (የቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  2. ተጫራቾች ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች እና ሎት 4 የፈርኒቸር ዕቃዎችን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡ የዞኑ አድራሻ ምዕ/ጎንደር ዞን ገንደ-ውሃ ከተማ ከአቢሲኒያ ባንከ 3ኛ ፎቅ ላይ ይገኛል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንከ የተረጋገጠ ሊትር ኦፍ ክሬዲት ወይም በገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ መሂ 1 በተቆረጠ በጥሬ ገንዘብ ሁኖ የጠቅላላ ገዥውን ዋጋ 2 በመቶ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ግዡን ዋጋ ገቢ በማድረግ ከፖስታ ውስጥ ማስገባት ወይም በተጫራቾች የሚሞላውን የጨረታ ማስከበሪያ ቅፅ ሞልቶ ማቅረብ  አለባቸው፡፡ የጨረታ ሰነዱን ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. የመጫረቻ ሰነድ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታውን ለመገምገም በርካታ ጊዜ ለማይወስዱና ውስብስብ ላልሆኑ ገዥዎች ከ40 ቀናት መብለጥ እንደሌለበት እያወቁ የመጫረቻ ሰነድዎን መሙላት አለብዎት፡፡
  5. ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታ ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለተጨማሪ ውል አስኪቋረጥ ድረስ ለሚቆይ 20 ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም እንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በምዕ/ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ገዥና ንብረት አስ/ቡድን መሪ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ስዓት ከህዳር 22/ 2018 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 06/2018 ዓ/ም ድረስ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
  7. ጨረታው ታህሳስ 07/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4:30 በገንደ ውሃ ከተማ በምዕ/ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ በግዥን ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግልጽ ይከፈታል፡፡
  8. አሽናፊው የሚለየው በሎት በጥቅል ድምር ስለሆነ የእያንዳንዱ ዝርዝር ዋጋ መሞላት አለበት፡፡ ካልተሟላ ግን ከጨረታ ውጭ የሚሆኑ መሆኑን አንገስፃለን፡፡
  9. በጨረታ ሰነድ ላይ ከተቀመጠ የዋጋ መሙያ ፎርም በስተቀር በማሳሰቢያ የሚሞላ ዋጋና ስርዝ ድልዝ ያለበት እንዲሁም የማይነበብ ጽሑፍ ተሞልቶ ከቀረበ የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  10. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ የሚከፈትበት ሰዓት እንደተጠቀ ሆኖ በቀጣይ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  11. ግዥ ፈፃሚ አካል የጨረታውን አሸናፊ በሚመርጥበት ጊዜ መለኪያዉ ተለይቶ የሚታወቅ እስከ ሆነ ድረስ በእያንዳንዱ የዕቃ መለኪያ የተሰጠውን የነጠላ ዋጋ ወይም ሌሎች የውል ቃሎችን እና ሁኔታዎችን ሳይለውጡ የእቃውን ብዛት ወይም መጠን እስከ 20 በመቶ ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል፡፡
  12. አሸናፊ ድርጅት የውል ማስከበሪያ የሞላውን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንት ወይም (ሲፒኦ) በማስያዝ በምዕ/ጎንደር ዞን በቃቢ ህግ መምሪያ በመቅረብ ውል መውሰድ የሚችል፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ሆኖም የምክንያቶቹን አግባብነት እንዲያስረዳ አይገደድም፡፡
  14. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ – በአካል በመገኘት ወይም በስልክ 058 331 08 80 /058 331 06 32 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here