ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
151

የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ በመደበኛ እና ከተለያዩ  ፕሮግራሞች በተገኘ  በጀት ለሥራ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የውሀ ማጣሪያ ቦትል፣ ሎት 2 የውሀ ማከሚያ ኬሚካሎች፣ ሎት 3 የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያ  ሎት 4 ብስክሌትና የብስክሌት ጎማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርት የምታሟሉ ሁሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  2. የግዥው መጠን በየንግድ ዘርፉ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ሎት  01  እና 02 ሎት   ለተዘረዘሩት ለእያንዳንዳቸው 40,000.00 /አርባ ሺህ ብር/ ለሎት 03  20,000.00  /ሀያ  ሺህ ብር/ እና ለሎት 4 ደግሞ 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/   በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ መይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. በጨረታው ፍላጎት ያላቸው ህጋዊ ድርጅቶች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የአብክመውሀና ኢነርጂ ቢሮ ቢሮ ቁጥር 23 በመቅረብ የማይመለስብር00 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚቻል ሲሆን ተጫራቾች ለመወዳደር የመወዳደሪያ ሰነዶችን ሲመልሱ የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም፤ ፊርማ እና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  7. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀንከቀኑ  8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ  ስዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ውሀና ኢነርጂ ቢሮ  ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግስት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልፆላቸው ቀርበው ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው በአግባቡ ባለመፈፀማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም የተወሰደው እርምጃ በማስረጃ የተደገፈ መሆን አለበት፡፡
  9. የማቅረቢያ ጊዜ ውል ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ15 ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ርክክብ የሚፈፅም ይሆናል፡፡ ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 0582220132 /0582201087 ዘወትር በሥራ ቀናት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  12. አድራሻ የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ/ ቀበሌ 07 ባህርዳር ዩንቨርስቲ ዊዝደም ፊት ለፊት

የአብክመ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here