ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
85

የአዲስ ዘመን ፖ/ቴ/ኮ/ ለ2018 ዓ.ም በጀት አመት የተለያዩ የማሰልጠኛ ለቢሮ እና ለቢሮ አገልግሎት የሚሆኑ እቃዎችን  ሎት1.ኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሎት2. የህንፃ መሳሪያዎች፣ ሎት3. የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት4. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት5. የደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ በጨረታው መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1.  ተጫራቾች በስራ ዘርፍ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ከመንግስት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና የሚሞሉት ዋጋ ከ200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በኮሌጁ ደረሰኝ ጥሬ ገንዘብ ገቢ በማድረግ ጠቅላላ የዋጋውን  ሁለት በመቶ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአ/ዘ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 ከህዳር 29/2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም እስከ 4፡00 ዘወትር በስራ ሰዓት በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ከፍለው መግዛት የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን ዋናውን በሁሉም ሰነዶች የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፣ ፊርማ እና ሙሉ አድራሻ በትክክል በመሙላት እና በደንብ ፖስታውን በማሽግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከተጠየቁት ማሰረጃዎች ጋር ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
  4. ሰነዱን ለሚገዙ ተጫራቾች ዝርዝር እና እስፔስፊኪሽን ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ ይቀርባል፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊው ድርጅት  ውል እንደያዘ ጨረታውን ላላሸነፉት ድርጅቶች ተመላሽ ይሆናል፡፡
  6.  አንድ ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
  7.  አሸናፊው በውሉ መሰረት ካላስረከበ መ/ቤቱ በግዥ መመሪያው መሠረት አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ይገደዳል፡፡
  8. አሸናፊው የሚለየው እንደ አስፈላጊነቱ በተናጠል ወይም በሎት (በጥቅል) ዋጋ ይሆናል፡፡.
  9. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10.  የጨረታው አሸናፊ  ዕቃውን በራሱ ትራንስፖት አ/ዘ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  11. አሸናፊው አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ  (አስር በመቶ) በማስያዝ ለተከታታይ 5 የስራ ቀናት ውስጥ ውል መውሰድ አለበት፡፡
  12. የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ15ኛው ቀን ማለትም ለታህሳስ 14/2018 ዓ.ም ከጧቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ እለት ከጧቱ 4፡15 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም የመክፈቻ ጊዜው አይራዘምም፡፡ በ15ኛ ቀን የበዓል ቀን እና  ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡00  ተዘግቶ በዚሁ እለት ከጧቱ 4፡30 በግልጽ ይከፈታል፡፡
  13.  ጨረታው ከብር 20,000/ ሃያ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ 3 በመቶ ቅድመ ግብር ክፍያ (ዊዝ ሆልድ) ታክስ ይቀነስበታል፡፡
  14. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 444 08 44 /162 በመደወል ወይም በአካል ቢሮ ቁጥር 9 በመቅረብ መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
  15. ማሳሰቢያ፣ ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተዘጋጀው ስፔስፍኬሽን ውጭ የራሱ ስፔስፍኬሽን ማስቀመጥ አይችልም፡፡

የአዲስ ዘመን ፖ/ቴ/ኮሌጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here