የጨረታ ቁጥር ARARI 01/03/2018
የአብክመ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የጽህፈት መሳሪያ ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች ፣ቋሚ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች፣ የመኪና ጎማ በጋዜጣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 119 በግንባር በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የሚገዙት ዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ተያይዟል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ዋጋ ለስቴሽነሪ 6500 ብር፣ ለፅዳት ዕቃዎች 5500 ብር፣ ለቋሚ የቢሮ ዕቃ 33000 ብር፣ እና ለመኪና ጎማና 13000 ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በግብርና ምርምር ኢንቲትዩት 1ኛ ፎቅቢሮ ቁጥር 120 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን ጧት 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ 16ኛው ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጠዋት 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ባለሙያዎች ክፍል ቢሮ ቁጥር 120 በ16ኛው ቀን ጧት በ3፡30 ተዘግቶ 4፡00 ላይ ይከፈታል፤ 16ኛው ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጠዋት በ3፡30 ተዘግቶ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ አሸናፊ ከሆኑ ያሸነፉበትን 10በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 120 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 226 60 77 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 50 74 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአብክመ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት

