በደቡብ ጎንደር ዞን የሰዴ ሙጃ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት ግን/አስ ቡድን በ2018 በመደበኛ በጀት የዶዘር ማሽን ኪራይ እና የፎቶ ግራፍና የእይታ መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በየዘርፉ ህጋዊ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈለና ቲን ነበር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን ፊርማቸውን አድራሻቸውን በድርጅቱ ስም የተዘጋጀ ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር በመክፈል ከመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 04 ዘወትር በስራ ቀን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ )ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ (በመሂ1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ 10በመቶ (አስር በመቶ) የውል ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ (በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ለ15 ተከታታይ ቀን በጋዜጣ ታትሞ ይቆያል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን በ3፡00 ይታሸጋል በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 2 ፣ 3፡30 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ጨረታውን ለመክፈት ቢገኙም ባይገኙም አይስተጓጐልም፡፡
- ከጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ውድቅ ይደረጋል።
- .ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- በጨረታ ማስታወቂያው ያልተገለጹ ካሉ በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆኑ እና ለወደፊቱም በመንግስት ጨረታ እዳይሳተፉ ይደረጋል፡፡
- የጨረታ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ (ማሻሻያ) ማድረግና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 09 15 29 02 08 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የሰዴ/ሙ/ወ/ ገንዘብ/ጽ/ቤት

